Time for change

No bullet can stop the spirit of justice and democracy!!!

Archive for the month “December, 2012”

Sew Le Sew Drama: “Disagreement” brewing between Producers and Actress

Read more : http://www.amharictube.com/article_read.php?a=149

posted by Gheremmew Araghaw

የጎልጉል ቅምሻ (ከዚህም ከዚያም)

ብልቴን ሰረቁት

በምስራቅ ቻይና የዢያንግ አውራጃ የኒቂያዖ ፖሊስ የደረሰው ክስ ግራ የሚጋባ ሆኗል፡፡ የ41ዓመቱ ፌ ሊን “ተኝቼ ሳለ ሌቦች ክፍሌ በርግደው በመግባት ብልቴን ሰረቁት” በማለት ነበር ወንጀሉን ያብራራው፡፡ ሲቀጥልም ሌቦቹ ቤቱ እንደገቡ ጭንቅላቱ ላይ የሆነ ነገር አድርገው ሱሪውን ወደታች ካወረዱ በኋላ ሮጠው እንደጠፉ አስረድቷል፡፡ “በጣም ከመደንገጤ የተነሳ ምንም የተሰማኝ ነገር አልነበረም፤ በኋላ ግን እየደማሁ መሆኔን ሳስተውል ብልቴ ተበጥሶ መሄዱን አስተዋልኩ” ብሏል፡፡

ፖሊስ እንደሚለው ሌቦቹ ሊን በሚያዘወትራቸው በርካታ ሴቶች የቀኑ አፍቃሪዎች ሊሆኑ እንደሚችሉ ግምት በመስጠት ፍለጋውን ቀጥሏል፡፡ ሊን ግን ይህንን የፖሊስ መላምት ካለመቀበል በተጨማሪ የትም ሂያጅ ሳይሆን ታማኝ እንደሆነ ለራሱ ይመሰክራል፡፡ በስርቆቱ በርካታ አስተያየቶች እየተሰጡ ቢሆንም በርካታዎች ግን “የት አስቀምጦት ነው ሊሰረቅ የቻለው” በማለት የመከራከሪያ ጥያቄ ያቀርባሉ፡፡
ከፊልም ሙያ ወደ ምክርቤት
ታዋቂዋ የፊልም ተዋናይ አሽሊ ጀድ የዴሞክራቲክ ፓርቲን በመወከል ለአሜሪካ የህግ መወሰኛ ም/ቤት (ሴኔት) ልትወዳደር እንደምትችል በሰፊው እየተነገረ ነው፡፡ የባራክ ኦባማ ደጋፊ የሆነችው አሽሊ የምትወዳደረው ከኬንታኪ ጠቅላይ ግዛት ሲሆን ተፎካካሪዋም በመወሰኛው ም/ቤት የሪፓብሊካኑ ንዑሳን መሪ የሆኑት ሚች ማኮኔል ናቸው፡፡
አብዛኛውን የፊልም ኢንዱስትሪና ታዋቂነትን ይዛ ወደ ዘመቻ የምትገባው አሽሊ ውሳኔዋን አሳውቃ ለውድድር የምትቀርብ ከሆነ እጅግ በርካታ ደጋፊዎቿ ከሌሎች ጠቅላይግዛቶች በመምጣት ለምርጫ ዘመቻ በፈቃደኝነት እንደሚያገለግሉ ቃል እየገቡ ይገኛል፡፡
ከቶ አይቀር ሞቱ ምንም ቢረዝሙ
የዓለማችን ረጅሟ ሴት ቻይናዊቷ ያዖ ደፈን ከዚህ ዓለም በሞት ተለይታለች፡፡ የ39ዓመቷ ረጅም የዛሬ ሁለት ዓመት በዓለም የድንቆች መዝገብ የዓለማችን ረጅም ሴት በመባል ተመዝግባ ነበር፡፡ 7ጫማ ከ7ኢንች (2ሜትር ከ33ሴ.ሜ.) የምትረዝመው ያዖ የሞተችበትን ምክንያት የቻይና ዜና ባያስታውቅም የረጅምነት በሽታ (ጃይጋንቲዝም) እና ሌሎች ስትሰቃይ ቆይታለች፡፡
ወጣት ሳለች የቅርጫት ኳስ ትጫወት የነበረችው ያዖ በ15ዓመቷ 6ጫማ ከ7ኢንች (ሁለት ሜትር) ትረዝም ነበር፡፡ በበሽታ ትሰቃይ ከነበረችበት አልጋ ሆና “በፍጹም ደስተኛ አይደለሁም፤ ለምን ይህንን ያህል ረጅም ሆንኩ? ይህንን ያህል ባልረዝም ኖሮ ሰዎች እንደዚህ አይመለከቱኝም” በማለት የዛሬ ሦስት ዓመት ሃዘኗን መግለጽዋ ተዘግቧል፡፡
“አላሁ አክበር” በቤተክርስቲያን
የሙስሊም ሕዝብ ጉዳዮች ምክርቤት (MPAC) ለመጀመሪያ ጊዜ ዓመታዊውን ስብሰባ በቤተክርስቲያን ሊያደርግ ነው፡፡ በፓሳዴና ካሊፎርኒያ በሚገኘው የሁሉም ቅዱሳን ኤጲስቆጶሳዊ ቤ/ክ (All Saints Episcopal Church) እንደሚካሄድ የተነገረለት ይኸው የሙስሊሞች ስብሰባ እጅግ ከፍተኛ ተቃውሞ እየደረሰበት ይገኛል፡፡
“በመቻቻል ስም ኢስላሚስቶች ጅል በሆኑ ክርስቲያኖች እየተጠቀሙ ነው”፤ “የአገራችንን (የአሜሪካንን) ሕገመንግሥት ለማፍረስና የሻሪያ ሕግ ለማስፈን ከሚሰራ ድርጅት ጋር በማበር የአገሬንና የልጅ ልጆቼን መጻኢ ዕድል አደጋ ላይ በመጣላችሁ ተጠያቂዎች ናችሁ” የሚሉ ጠንካራ መልዕክቶች የደረሷቸው መሆኑን የገለጹት የቤክኑ አስተዳዳሪዎች ስብሰባው በተሳካ ሁኔታ እንዲካሄድ የደኅንነትና የፖሊስን ድጋፍ እየጠየቁ ይገኛሉ፡፡ የምክርቤቱ ፕሬዚዳንት ሳላም አልማራያቲ “እንደቀድሞው ሁሉ ስብሰባውን በሆቴል ወይም በስብሰባ አዳራሽ ማድረግ እንችል ነበር፤ ሆኖም ቤ/ክ ውስጥ ማድረጋችን ም/ቤታችን ለሰላም እና ፍትሕ የቆመ ለመሆኑ ማሳያ እንዲሆን በመፈለጋችን እና ለሙስሊሞችም እርስበርሳቸው እየተነጋገሩ ችግራቸውን ይዘው ከሚኖሩ ለአብዛኛው የአሜሪካ ሕዝብ መልዕክታቸውን እንዲያደርሱ ታስቦ የተደረገ ነው” ይላሉ፡፡ አክራሪ የክርስቲያን ተቋማት መሪዎች የሙስሊሙን ም/ቤት በእጅ አዙር ለአሸባሪዎች ዕርዳታ የሚሰጥ ራሱ አሸባሪ የሆነ ድርጅት ነው በማለት ይከስሳሉ፡፡ የመንግሥትና ሃይማኖትን ጥምረት የሚቃወሙም እንዲህ ዓይነቱን የመንግሥት ድጋፍ የሚሰጠው ሃይማኖታዊ እንቅስቃሴ አጥብቀው ያወግዛሉ፡፡
ከ6ሴቶች 9ልጆች
በአሜሪካ የዊስኮንሲን ጠቅላይግዛት ነዋሪ የሆነው ኮሪ ከርቲስ ከስድስት የተለያዩ ሴቶች ዘጠኝ ልጆችን በመውለዱ ቤተሰቡን በሚገባ ማስተዳደር እስከሚችል ድረስ “መራባት እንዲያቆም” ፍርድቤት ወስኖበታል፡፡
ወደ 90ሺህ ዶላር ያልተከፈለ የልጆች ማሳደጊያ ድጎማ ዕዳ ያለበት የ44 ዓመቱ ዕዳውን ከፍሎ እስኪጨርስ ድረስ 10ኛ ልጅ መጨመር እንደማይችል ዳኛው ማስጠንቀቂያ ሰጥተውታል፡፡ በተመሳሳይ ሁኔታ በኬንታኪ ጠቅላይ ግዛት ከ11ሴቶች 12ልጆችን የወለደውን “አቶ ዘረብዙ” 13ኛ ልጅ እንዳይጨምር መራባት እንዲያቆም የወሰኑበት ዳኛ በአመክሮ በሚቆይበት ከ1 እስከ 5 ዓመታት ጊዜ ውስጥ ከወሲብ እንዲታቀብ ትዕዛዝ ሰጥተውታል፡፡ የሁለቱም ፍርድቤት ውሳኔዎች አፈጻጸም ግን በውል አልታወቀም፡፡
ፕሬዚዳንት ሂላሪ ክሊንተን?
የዛሬ አራት ዓመት ለፕሬዚዳንትነት ፓርቲያቸውን ወክለው በመወዳደር በባራክ ኦባማ የተሸነፉት ሂላሪ ሮድሃም ክሊንተን በ2016 ዳግም ለፕሬዚዳንትነት ይወዳደራሉ የሚል ወሬ በስፋት እየተናፈሰ ነው፡፡ በቅርቡ በተጠናቀቀው ምርጫ የተሸነፉ የፓርቲያቸውን እጩዎች የሚያበረታታ በራሳቸው እጅ የተፈረመ ደብዳቤ መላካቸው በተንታኞች ዘንድ በቀላሉ አልታየም፡፡ ምዕራብ ኒውዮርክን በመወከል ለተወካዮች ም/ቤት ተወዳድረው በጠባብ ውጤት ለተሸነፉት ኔት ሺናጋዋ በላኩት ደብዳቤ ላይ በአሁኑ ምርጫ ቢሸነፉም በቀጣይ ዓመታት በህዝባዊ መድረኮች ላይ የእርሳቸውን ድምጽ እንደሚሹ ሂላሪ ክሊንተን ጠቁመዋል፡፡
ባራክ ኦባማ በዚህኛው የምርጫ ዘመቻቸው መሪቃል ወደፊት (Forward) የሚል እንደነበር ሁሉ ሂላሪ ክሊንተን በደብዳቤያቸው ላይ “Onward” በማለት የጠቀሷት ቃል ምናልባት የምርጫ ዘመቻቸው የመፈክር ቃል ትሆን የጎልጉል ግምት ነው፡፡ መቆየት ደጉ ብዙ ያሰማናል፡፡
ባለሦስት እግሩ በራሪ
የሥራ ሰዓት ሲረፍድ፤ ታክሲ ሲጠፋ ወይም መንገዱ በትራፊክ ሲጨናነቅ፤ ሰዓቱ ሲበር በሰማይ መብረር ያሰኛል፡፡ በእርግጥ መብረር ይቻላል፡፡
መፍትሔው 75ሺህ ዶላርና የፓይለት መንጃፈቃድ ማውጣት ብቻ ነው፡፡ ከዚያ አንዴ ነዳጅ ሞልቶ ለ5ሰዓታት መብረር ነው – በበራሪው ባለሦስት እግር፡፡
ሳቅ በሳቅ LOL
ለሦስት ዓመታ በከንፈር ወዳጅነት ከቆዩ በኋላ ከሦስት ወር በፊት ሲለያዩ ለወንድየው ቀላል የሆነው መለያየት ልጅቷን አእምሮዋን በማሳት ወደ ወንጀል መርቷታል፡፡ በቴክሳስ ጠቅላይግዛት ነዋሪ የሆነችው ኤልሳቤጥ ማክሌይን ከወንድ ጓደኛዋ ከተለያየች በኋላ ህይወቱን ቀውጢ በማድረግ በቀን እስከ መቶ ጊዜ ስልክ ትደውልለት ነበር፡፡ ጉዳዩ ያሳሰበው ወጣትም ለፖሊስ ያመለክታል፡፡
እርሷም ከተለያዩ ስልኮች መደወሏንና ማስፈራራቷን ቀጠለች፡፡ በቀን እስከ 750 ጊዜ ድረስ በመወደልና በአንድ ጊዜ እስከ 126 አጭር ፈጣን መልዕክት (ቴክስት) በመላክ ህይወቱን መቅኖ ቢስ አደረገችው፡፡ ከጥቂት ቀናት በፊት ግን የልጁን እናት በመኪና በመግጨት ወደ መንገድ ከጎተተቻት በኋላ በሞትና ህይወት መካከል ጥላት ለቀድሞው የከንፈር ወዳጇ “ህይወት እንዴት ነው ሳቅ በሳቅ (LOL)” በማለት አጭር መልዕክት ትልካለች፡፡ እናትየው በርካታ የአጥንት ስብራትና ጉዳት ደርሶባት በህክምና የእየተረዳች ሲሆን ኤልሣቤጥ በወንጀል ተከስሳ የ65ሺህ ዶላር የገንዘብ ዋስ ተበይኖባታል፡፡
http://www.goolgule.com/sweet-golgul-4/

posted by Gheremew Araghaw

‹‹አሜሪካ የመጣሁት ከቃሊቲ ስለሚሻል ብቻ ነው›› ዳዊት ከበደ (የቀድሞው የአውራምባ ታይምስ ጋዜጣ ማኔጂንግ ኤዲተር)

‹አሜሪካ የመጣሁት ከቃሊቲ ስለሚሻል ብቻ ነው››
ዳዊት ከበደ
የቀድሞው የአውራምባ ታይምስ ጋዜጣ ማኔጂንግ ኤዲተር

በ97 ዓ/ም. በሀገራችን ተከስቶ በነበረው ፖለቲካዊ ቀውስ ሣቢያ ለእስር ከተዳረጉ ጋዜጠኞች መካከል አንዱ ነው፡፡ ከአንድ ዓመት ከዘጠኝ ወራት እስር በኋላ በሂደት አውራምባ ታይምስ ጋዜጣን በየካቲት ወር 2ዐዐዐ ዓ.ም. አቋቁሞ ማሳተም ጀመረ፡፡ የሲፒጄ የ2ዐ1ዐ የኘሬስ ነፃነት ዓለም አቀፍ ተሸላሚ የነበረው – ጋዜጠኛ ዳዊት ከበደ፡፡ ህዳር 9 ቀን 2ዐዐ3 ዓ/ም. ግን “ይቅርታዬ ተነስቶ እንድታሠር በመወሰኑ ከፍትህ ሚኒስቴር አስተማማኝ ምንጭ መረጃ አገኘሁ” በማለት ከሀገሩ ወደ አሜሪካ መሰደዱ ይታወሳል፡፡
ኤልያስ ገብሩም ለቀድሞው የአውራምባ ታይምስ ጋዜጣ ማኔጂንግ ኤዲተር ጋዜጠኛ ዳዊት ከበደ በተለያዩ ርዕሠ ጉዳዮች ዙሪያ ጥያቄ በማንሣት ተከታዩን ቃለ-ምልልስ አድርጓል፡፡

 አድዋ እንደተወለድክ አውቃለሁ፤ እስቲ ስለትውልድህና ስለልጅነት ህይወትህ ጠቅለል አርገህ ንገረኝ፡፡ አድዋ በመወለድህስ ምን ይሰማሀል?

በቅድሚያ እድሉን ስለሰጣችሁኝ እጅግ በጣም አመሰግናለሁ፡፡ ያው የተወለድኩት አድዋ
ነው፡፡ ያደግኩት ደግሞ አዲስ አበባ፡፡ አንዳንድ ሰዎች አድዋ መወለዳቸውን ብቻ እንደ ትልቅ ስኬት አድርገው ይቆጥሩታል፡፡ እኔ ግን አይታየኝም፡፡ ሰው ፈልጎ ባመጣው ነገር ነው መኩራት ያለበት፡፡ እውነትም ፈልጌና መርጬ አድዋ ብወለድ ኖሮ እንደ ስኬት እቆጥረው ነበር፡፡ በተረፈ ከተወለድኩ በኋላ ነው የት እንደተወለድኩ ያወቅኩት፡፡ ስለዚህ አጋጣሚ እኔ የተወለድኩበት አካባቢ የተወለዱ ጠቅላይ ሚኒስትር ኢትዮጵያን ለ21 ዓመታት ስለመሩ የዚህ ኩራቱ አይታየኝም፡፡ ከዛ ይልቅ መኩራት ያለብኝ አድዋ ላይ በተሰራው የጥቁር ህዝቦች ታላቅ ታሪክ ነው፡፡ ያ ታሪክ ደግሞ በሌላ የኢትዮጵያ ክፍልም ብወለድ ኖሮ ኩራቱ እኩል ነው የሚሰማኝ፡፡

ጋዜጠኝነትን መቼ ጀመርከው? ወደዚህ ሙያ እንድትገባስ ምክንያት የሆነህ ምንድነው?

ጋዜጠኝነትን መቼ እንደጀመርኩት ከመናገር ይልቅ፤ ለሙያው ትኩረት መስጠት የጀመርኩት ከመቼ ጀምሮ እንደሆነ መናገሩ ይሻላል፡፡ የጋዜጠኝነት ፍቅር በውስጤ ማደር የጀመረው ገና የአራት አመት ልጅ እያለሁ ጀምሮ ነው፡፡ በወቅቱ ምንም የማውቀው ነገር ባይኖርም አባቴ አንድ አነስተኛ ሬዲዮ ይዞ የአሜሪካ ድምጽ ሬዲዮ በተመስጦ ሲሰማ በጣም ይገርመኝ ነበር፡፡ እና አስታውሳለሁ፡- በወቅቱ ለእኔ በጣም አስገራሚ የነበረው ‹‹እንዴት ነው የሰው ልጅ በእንደዚህ አይነት ትንሽዬ ነገር ውስጥ ሆኖ (ሬዲዮውን እያየሁ ማለት ነው)  ሊያወራ የሚችለው›› የሚለው ነገር ነበር፡፡ ደግሞም በነገሩ ተገርሜ ዝም አልልም” አባቴንም እጠይቀው ነበር፡፡ ታዲያ ሁሌ እሱ በተመስጦ ሲሰማ እኔ ደግሞ ያንኑ ተመሳሳይ ጥያቄ ደጋግሜ እየጠየኩ ሳስቸግረው አንድ ቀን ‹‹ስማ ጋዜጠኞች ናቸው፤ የሚያወሩት እዚህ ውስጥ ገብተው ሳይሆን ሌላ ቦታ ሆነው ነው፡፡ ስለዚህ እንደነሱ መሆን ከፈለክ ትምህርትህን ጠንክረህ ተማር!›› አለኝ፡፡

ከዛ በኋላ በትምህርት ቤት ግጥም ማንበብ፣ የተለያዩ ክበባት ውስጥ መግባት፣ ሚኒ ሚዲያ መሳተፍ ጀመርኩ፡፡ 12ኛ ክፍል ጨርሼ የማትሪክ ውጤት እስኪመጣልኝ ድረስ ባለው የክረምት ወር ከአዲስ አበባ ማስታወቂያ ቢሮ የሦስት ወር የጋዜጠኝነት ስልጠና ወሰድኩ፤ እግረመንገዴንም በአንዳንድ ጋዜጦችና መጽሄቶች ጽሁፍ እንዲወጣልኝ መስጠት ጀመርኩ፡፡ ከዚህ በኋላ የማትሪክ ውጤት መጣ፡፡ የመጣው የማትሪክ ውጤት በመንግስት የትምህርት ተቋም ሊያስገባኝ የሚችል ቢሆንም እኔ ግን ሁሌ የማስበው ጋዜጠኝነት ብቻ ስለነበረ በወቅቱ የጋዜጠኝነት ትምህርት የሚሰጠውን ዩኒቲ ኮሌጅ መርጬ ገባሁ፡፡ እና በዚህ መልኩ ነው ወደ ሙያው የገባሁት፡፡

 

በጋዜጠኝነት ህይወትህ ውስጥ የገጠመህን ፈተናና ውጣ ውረድ ብትገልጽልን? (ከሐዳር ጋዜጣ ጀምሮ እስከ ፊኒክስ – አሪዞና ድረስ የነበረህን ጉዞ ብትነግረን)

እንግዲህ ፈተና ሲባል ከትልቁ ነው መጀመር ያለብኝ፡፡ እኔ መጀመሪያ ያጋጠመኝ ፈተና ትልቁ ፈተና ነው፡፡ እስኪ አስበው በአንድ የክስ መዝገብ ውስጥ በስድስት የተለያዩ ክሶች መከሰስ ብቻ ሳይሆን” የእያንዳንዱ ክስ ቅጣት ደግሞ እድሜ-ልክ እና ሞት የሚያስፈርድ ሲሆን ምን አይነት ፈተና ብለህ ትጠራዋለህ? የ1997ቱን ፈተና ዱብ እዳ ከማለት ውጪ ምን ትለዋለህ፡፡ ደግሞም ከዛ በፊት ታስሬ አላውቅም፡፡ አንዳንዴ ፕሬስን የመሰለ ተቋም በአንድ አገር ሊኖረው የሚገባው ሚና እጅግ በጣም ትልቅ ቢሆንም” ይህ አይነቱ ተቋም ድምጥማጡ እንዲጠፋ የሚያደርግ ፍጹማዊ ስልጣን በጣም ጥቂት በሆኑ ግለሰቦች እጅ ውስጥ ገብቶ እንዳሻቸው ሲጫወቱበት ታያለህ፡፡ ሙያውና ሙያተኛው የሚተዳደርበት ህግን የሚያረቁት እነሱ፣ ሙያተኛም ተሰብስቦ እስር ቤት እንዲገባና በሞት እንዲቀጣ አቃቤ ህግ ሆነው የሚከራከሩት እነሱ፣ የአለም የፕሬስ ቀን በተከበረ ቁጥርም ይሁን በተለያዩ ኮንፈረንሶች ተገኝተው ‹‹የኢትዮጵያ ጋዜጠኞች ያላቸው የኤዲቶሪያል ነጻነት ለአለም ሁሉ ምሳሌና ትምህርት ይሆናል›› የሚል ስብከት የሚሰብኩትም እነሱ ናቸው፡፡ አየህ ኢንዱስትሪው ኃላፊነት እንዲሰማው ለማድረግ ሁሉንም የሚያስማማ ግልጽ የሆነ ተቋማዊ አደረጃጀትና ሁሉም በእኩል የሚስተናገዱበት ጽኑ መሰረት ያለው የህግ ማዕቀፍ ሊኖር ይገባል፡፡ አለበለዚያ ግለሰቦች  እንዳሻቸው በታማኝነት አሊያም በቂም በቀል ውሳኔ የሚያስተላልፉበት፤ በየጀበና ቤቱ ማን ፍቃድ ሊነጠቅ እንደሚገባ፣ ማን መባረር እንዳለበት የሚወስኑበት አገር ነው ያለን፤ ያሳዝናል፡፡

ጥያቄውን በትክክል አልመለስክልንም?

ያው ስለውጣ-ውረድ ነው እየጠየቅከኝ ያለኸው፡፡ ከአዲስ አበባ እስከ አሪዞና ድረስ ያለውን መንገድና ውጣ-ውረድ መዘርዘር አቅቶኝ አይደለም፡፡ ከዚህ ሁሉ ውጣ-ውረድ እና እንቅፋት በስተጀርባ ያለው መነሻ ምክንያት ምን እንደሆነ ነው መታወቅ ያለበት፡፡ አውራምባ ውስጥ ዘገባዎችን ሚዛናዊ ለማድረግ ምን ያህል ርቀት ስንጓዝ እንደነበር ታውቃለህ፡፡ ያንን እያደረግን ግን የግል ጥላቻ የነበራቸው ሰዎች ነበሩ፡፡  በመንግስታዊ መዋቅር ውስጥ ያላቸው ‹‹ስልጣን›› ደግሞ የግል ጥላቻቸውን ለማራመድ ምቹ ነበር፡፡ እናም ያላቸውን ኔትወርክ ተጠቅመው ሳንወድ በግዳችን ከጨዋታው እንድንወጣ አደረጉን፡፡ ከኮሚኒኬሽን ጽህፈት ቤት እስከ ፍትህ ሚኒስቴር፤ በጉዳይ ፈጻሚነት ከሚያገለግሏቸው የግል ሬዲዮኖች፤ እስከ መንግስታዊው አዲስ ዘመን ድረስ ተረባርበው ስራቸውን ሰሩ፡፡ ከዛ ደግሞ ክራቫታቸውን አሳምረው በኪሳራ እንደዘጋነው ሊሰብኩ አለም አቀፍ ሚዲያዎች ላይ ወጡ፡፡ ስለዚህ የውጣ-ውረዱ ማጠንጠኛ እዚህ ላይ ነው ያለው፡፡

አሁን ባለህበት አገር አሜሪካ ኑሮን እንዴት እየገፋኸው ( እየመራኸው) ነው? ለመሆኑ ምግብ ታበስላለህ?

ማንም እንደሚያውቀው ተገድጄ ነው የወጣሁት፡፡ በተደጋጋሚ እንደገለጽኩት አሜሪካ የመጣሁት ከቃሊቲ ስለሚሻል ብቻ ነው፡፡ የመንግስት ደጋፊ የሆኑ ወዳጆቻችን እንደሚሉት ሰው የሚሰደደው የተሻለ ኑሮ ለመኖር ነው፡፡ እኔ ያየሁት የተሻለ ኑሮ ምን እንደሆነ አላውቅም፡፡ ከሙያዬ ውጪ ሌላ ስራ እንኳን መስራት አልፈልግም፡፡ በመንፈስ ደረጃ ስደትም ሌላ እስር ቤት ነው፡፡  እንደምታውቀው ከአገሬ የወጣሁት በ 2004 ህዳር ወር መጀመሪያ ላይ ነው፡፡ ሁኔታዎች ይሻሻላሉ በሚል ተስፋ እስከ መጋቢት ድረስ    የ‹‹አሳይለም›› (የጥገኝነት) ጥያቄዬን አላቀረብኩም ነበር፡፡ በኋላ ግን የግድ የሚዲያ ስራውን ስደት ላይ ሆኜ መቀጠል ስለነበረብኝ ህጋዊ የሆነ ማዕቀፍ ውስጥ ለመግባት ‹‹አሳይለም››(ጥገኝነት) ከመጠየቅ ውጪ ሌላ አማራጭ አልነበረኝም፡፡ ስደት ካከበድከው ይከብዳል” ካቀለልከውም ይቀላል፡፡ ምግብ አበስላለሁ፡፡ አንዳንዴ ደግሞ ሲሰለቸኝ ውጭ እመገባለሁ፡፡

እንደሚታወቀው አሁን ድረ-ገፅ አቋቁመሃል፤ ስራው አንዴት ነው? (ከጋዜጣ ስራ የሚለይበት ነገርስ ምንድን ነው?)

የድረ-ገጽ ስራ ከጋዜጣ ይለያል፡፡ ጋዜጣ በሳምንት አንዴ ነው የሚታተመው፡፡ ድረ-ገጽ ግን በየሰዓቱ የሚፈጠሩ አዳዲስ ነገሮችን እየተከታተልክ ማቅረብ የግድ ይላል፡፡ ሌላ ዌብ ሳይት ቀድሞ ሳያወጣው የመጀመሪያ ለመሆን የምታደርገው ትንቅንቅ ደስ ይላል፡፡ ለምሳሌ ከዌብሳይቶች መካከል የብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስን ህልፈት፤ የአቶ መለስን ዜና እረፍት (ከኢቲቪ ቀጥሎ) ቀድሞ ያወጣው ዌብሳይት አውራምባ ነው፡፡ ለምሳሌ ኦባማ በድጋሚ ተመረጡ ተብሎ በቀጥታ (ላይቭ) ሲነገር በ1 ደቂቃ ከ 15 ሴኮንድ ውስጥ ዜናውን ፖስት በማድረግ አውራምባ የመጀመሪያው ነው፡፡ የእድል ጉዳይ ሆኖ የአውራምባ ድረ-ገጽ በተመረቀ በሁለት ወር ውስጥ ነው ከፍተኛ ጎብኝ ካላቸው አንጋፋ ድረ-ገጾች መካከል አንዱ ለመሆን የበቃው፡፡ የዳያስፖራ የፖለቲካ ሙቀት ከምትገምተው በላይ ነው፡፡ ነገሮችን በኃላፊነት መንፈስ መርምረህ ገለልተኛ የሆኑ አቋሞችና አመለካከቶችን መያዝ ካልቻልክ ፈታኝ ነው፡፡ ልክ አገርቤት ‹‹በዚህ ጉዳይ ላይ መዘገብ የለብህም›› የሚሉ አምባገነኖች እንዳሉ ሁሉ፤ እዚህም በተመሳሳይ መልኩ እኛ የምንፈልገው ነገር ብቻ ነው መቅረብ ያለበት የሚሉ ‹‹የዳያስፖራ ሽመልስ ከማሎች›› አሉ፡፡ ልክ አገር ቤት ጸያፍ ስድብ የሚሳደቡ የሬዲዮ ጣቢያ ባለቤቶች እንዳሉ ሁሉ እዚህም በመልክም በተግባርም እነሱን የሚመስሉ በሌላ ጽንፍ የተሰለፉ የፓልቶክ አድሚኖች አሉ፡፡ ይገርምሀል እንዲሁ ፈርዶብን የአምባገነንነት ችግር የትም ቦታ ነው የሚያጋጥመን፡፡ እጅ ላለመስጠት ቁርጠኛ መሆን ግን ግድ ይላል፡፡

ከዲሲ ወደ ኦሪዞና ግዛት ለምን ሄድክ? (ብዙ ኢትዮጵያውያን ካሉበት መራቁ ለስራህ ጥሩ ነው?)

አዎ! ዲሲ ብዙ ኢትዮጵያዊያን አሉ፡፡ የብዙ ፖለቲከኞችና ቲፎዞዎቻቸው መፈንጫ፤ የብዙ ፍላጎቶች መናኸሪያም ነው፡፡ ብዙ ዝግጅቶች፣ በርካታ ሰላማዊ ሰልፎችና ኮንፈረንሶችም ይከናወንበታል፡፡ ይህ ማለት ግን አገር ቤት ለሚደረገው ትግል አሊያም እንዲመጣ ለምንፈልገው ፖለቲካዊ መቻቻል የሚኖረው ፋይዳ እዚህ ግባ የሚባል አይደለም፡፡ በኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ ጽንፍ የያዘ የፖለቲካ አማራጭ አሉታዊ እንጂ አዎንታዊ ውጤት የለውም፡፡ ገና ለገና ነጻነት ያለበት አገር ላይ ነው ያለነው ተብሎ የሚደረገው ልቅ የሆነ የመጠፋፋት ዘመቻ፤ ገና በዳዴ ላይ ላለው የፖለቲካ ባህላችን መራዥ የሆነ ሚና ነው የሚኖረው፡፡
ስለዚህ ከዲሲ ወደ አሪዞና የመጣሁበት ዋናው ምክንያት ከዚሁ ጋር በተያያዘ ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ እዚሁ አሪዞና ስቴት ዪኒቨርስቲ ትምህርቴን ለመቀጠል አንዳንድ የሚያስፈልጉኝን ነገሮች እያሟላሁ ነው፡፡

የዳያስፖራውን ኑሮ፣ ማህበራዊ-ህይወትና፣ ፖለቲካ እንዴት ተመለከትከው? በተለይ ፖለቲካ አራማጆቹ የፅንፈኝነት ደረጃቸውን እንዴት ትገልጸዋለህ? የዳያስፖራ ፖለቲካ ሲባል ሚዲያዎቹንም ይመለከታልና አያይዘህ ብትመልስልኝ፡-

እንደው አለመታደል ሆኖ የፖለቲካ ባህላችን ከ1960ዎቹ ጀምሮ የጽንፍ ፖለቲካ ነው፡፡ የኢህአዴግ ደጋፊዎችም ሆኑ ተቃዋሚዎች በእኩል ደረጃ ሁለት ጫፍ ይዘው ነው ሲጠዛጠዙ የምታያቸው፡፡ ፍልሚያው ደግሞ በኢህአዴግና በተቃዋሚዎች መካከል ብቻ የሚቆምም አይደለም፡፡ አንዱ ተቃዋሚ ሌላውን በወያኔነት ለመፈረጅ ያለው ጥድፊያ ብዙ መጽሐፍ ይወጣዋል፡፡ <የአንድን ሰው የፖለቲካ አቋም ለመፈረጅ ብሄሩን ጠንቅቀህ ማወቅ በቂ ነው> ባዬች ብዙ አሉ፡፡ አንዳንዴ አገር ቤት ያለው እንዴት አይነት ስልጡን ህዝብ ነው ትላለህ፡፡ ሁለቱም ወገን ጋር የምትመለከተው ‹‹እኔ ጋ ካልሆንክ ጠላቴ ነህ›› አይነት አጥፊ ድምዳሜ ነው፡፡
ሚዲያዎቹም የዚህ አይነቱ አሰላለፍ ሰለባዎች ናቸው፡፡ በተለይ እዚህ የምታየው አስቀያሚ ነገር የፖለቲካ ልዩነትን የብሄር ካባ አልብሶ ድምዳሜ ላይ ለመድረስ ያለው ሩጫ ተአምር ነው፡፡ አንድ የፖለቲካ ድርጅት ‹‹ጸባችን ከስርዓቱ ጋር ነው” ከትግራይ ህዝብ ጋ አይደለም›› ሲል ትሰማውና ትንሽ ቆይቶ ደግሞ ‹‹አጼ ዮሐንስም እኮ ለአካባቢያቸው ተወላጆች ነበር ስልጣን የሚሰጡት፤ እነ ብርሀነ መስቀልና እነ ተስፋዬ ደበሳይም ለትግራይ የበላይነት ነው ሲታገሉ የኖሩት›› ሲሉ ትሰማቸዋለህ፡፡ ይህ አይነቱ አባባል ‹‹ጸባችን ከህዝቡ ጋር ሳይሆን ከስርአቱ ጋር  ነው ለሚለው ፕሮፖጋንዳ እንዴት ግብአት ሊሆን እንደሚችል ግልጽ አይሆንልህም፡፡
እንደሚገባኝ ከሆነ ይህ አይነቱ የፖለቲካ ስትራተጂ ተግባራዊ እንዲሆን የተፈለገው ‹‹ህወሃት በትጥቅ ትግሉ ወቅት ደርግና አማራ አንድ እንደሆኑ አድርጎ ይቀሰቅስ ነበር፤ እናም በዚህ መንገድ ውጤታማ መሆን ችሏል›› በሚል የተሳሳተ ስሌት ምክንያት ይመስለኛል፡፡ ይህ አይነቱ የፖለቲካ ቀመር በ2012 ተግባራዊ ለማድረግ መሞከር ግን  ምንኛ ኋላ ቀር አካሄድ እንደሆነ ለመገንዘብ ዝግጁነቱ የለም፡፡ አንዳንዴ ከአንዳንድ የተቃዋሚ መሪዎች ጋር ሳወራ ‹‹የትግራይ ተወላጆች የጸረ ኢህአዴግ ትግሉን የማይቀላቀሉት ለምንድነው›› የሚል የቁጭት ጥያቄ ሲጠይቁ ይደመጣል፡፡ ነገር ግን ደግሞ እነ ስዬና እነ ገብሩ አስራት አይነት ሰዎች ወደ ተቃዋሚው ጎራ መጥተው ‹‹ተባብረን አንድ ነገር እናድርግ›› የሚል ጥያቄ ሲያቀርቡ የተቃዋሚው ምላሽ ‹‹እናንተም ያው ወያኔዎች ናችሁ›› የሚል ሆኖ ታገኘዋለህ፡፡ ‹‹ታዲያ እሺ ምን ይደረግ ስትል›› ደግሞ መልስ የለም፡፡

አሁን አቶ መለስ በህይወት የሉም፤ ወደአገርህ ለምን አትመለስም?

ችግሩ እኮ በአቶ መለስ መኖርና አለመኖር የሚፈታ አይደለም፡፡ ከሆነም እናየዋለን፡፡   አውራምባን የማዘጋቱና እኔን የማባረሩ የቤት ስራ የተሰራው ቀደም ብዬ እንደገለጽኩልህ ይህ አይነቱን ሴራ እንዲያከናውን በተመደበው ቡድን አማካኝነት ነው፡፡ ይህ ቡድን የሚያቀርበው ሪፖርት ደግሞ ከእንደኛ አይነቱ ምስኪን ዜጋ የበለጠ በአቶ መለስ ዘንድ አቅምና ተሰሚነት የነበረው ነው፡፡ አሁንም እንዳለው ይሰማኛል፡፡ ለዚሁ ተብሎ የተዋቀረ የጥፋት ቡድን ነውና፡፡

የአቶ መለስን ህልፈት ስትሰማ ምን ተሰማህ? በቀብራቸው ቀን ተገኝተው ሱዛን ራይስ ተናግረው ነበር፤ ንግግሩን እንዴት አየኸው?

በአቶ መለስ ህልፈት አዝኛለሁ፡፡ ለምን አዘንክ የሚለኝ ሰው ካለ በሱም ጭምር አዝናለሁ፡፡ አቶ በረከት ስምኦን ህልፈታቸውን በተመለከተ በይፋ ሲናገሩ ‹‹21 ዓመት ሙሉ ያለ እረፍት ሲሰሩ..ወዘተ›› ብለዋል፡፡ አዎ! በረከት ያሉት እውነት ነው፡፡ ኢትዮጵያ በአገር ቤትና በውጭ መለስን የሚተካ ሰው አጥታ አንድ ሰው እሰኪሞት ድረስ እንዲመራት ሲደረግ ያሳዝናል፡፡ አቶ መለስ ምንም ጥያቄ የለውም አዋቂ ናቸው፡፡ እንኳን አቶ መለስ አልበርት አንስታይንም 21 ዓመት ሙሉ አንድን አገር በብቃት መምራት አይችልም፡፡ አሜሪካዊያን ከስምንት አመት በላይ አንድ ሰው እንዲመራቸው የማይፈልጉት ለምንድነው? በቃ አንድ ሰው በሙሉ አቅምና ኃይል (ፓሽን) ውጤታማ (ፐሮዳክቲቭ) ሆኖ አገርን መምራት የሚችለው ለትንሽ ጊዜ ብቻ ነው፡፡ ወደ ኢህአዴግ ስንመጣ ለፖለቲካ መቻቻል በሩ ዝግ ነው፡፡ እሱ ብቻ ነው ለአገር የሚያስበው” ሌላው አገር አጥፊ ነው፡፡ ይህ የተሳሳተ የፖለቲካ ባህላችን ለጤናችን እንኳን ተገቢውን ጊዜ እንዳንሰጥ እያደረገን ነው፡፡ መለስ ብዙ ሰው አልቅሶ እንደቀበራቸው አውቃለሁ፡፡ ሁሉም ሰው ግን አልቅሶ አልቀበራቸውም፡፡ ያ ግን እንዲሆን ማድረግ ይችሉ ነበር” እድልም ነበራቸው፡፡
የሱዛን ራይስን ንግግር በተመለከተ በወቅቱ አንድ አርቲክል ጽፌ ነበር፡፡ መለስ ሱዛን ራይስ እንደገለጽዋቸው አይነት ሰው ቢሆኑ ኖሮ በሱዛን ራይስ አገር ላይ በጥገኝነት ተቀምጨ የሱዛን ራይስን ንግግር በቴሌቭዥን አልመለከተውም ነበር፡፡ መቅረጸ-ድምጼን ይዤ መስቀል አደባባይ ሆኜ ነበር የምመለከታቸው፡፡ እውነትም መለስ ‹ዓለም አቀፍ ደረጃ ያላቸው መሪ> <<ወርልድ ክላስ ሊደር›› ቢሆኑ ኖሮ እኔም እስክንድርም በቅድስት ስላሴ ካቴድራል ተገኝተን አልቅሰን እንሸኛቸው ነበር፡፡ ያ ግን አልሆነም፡፡ ለምን አልሆነም? ካልከኝ መለስ ሱዛን እንደገለጽዋቸው አይነት አይደሉማ!

አንዳንድ ወገኖች እዚሁ ሆነህ የሚከፈለውን ሁሉ መስዕዋትነት መክፈል እንደነበረብህ ይገልጻሉ፡፡ ምን ትላለህ ስለዚህ ጉዳይ?

በመጀመሪያ ጥያቄውን አታድበስብሰው! ‹‹እስካሁን ኢትዮጵያ ውስጥ ሰዎች በበቂ ሁኔታ አልታሰሩም” የእነ እስክንድር መታሰር በቂ ስላልሆነ አንተም መጨመር ነበረብህ›› ማለት ነው ጥያቄው፡፡ የኢትዮጵያ ህዝብ 80 ሚሊዮን ነው፡፡ እንደዚህ አይነት ጥያቄ የሚያነሱ ሰዎች ቀላሉን ጥያቄ ከመጠየቅ ከባዱንም ኃላፊነት ቢጋሩ መልካም ነው፡፡ ሌላው እንዲታሰር የምንጓጓውን ያህል የታሰሩትን ለማስፈታት ምን ጥረት አድርገናል ለመሆኑ? እስከ መቼ ነው ዋጋ የሚከፍሉልንን ሰዎች በመብራት እየፈለግን የምንኖረው? ሁሌ ተመሳሳይ ሰዎች ብቻ እየታሰሩ በይቅርታ እየወጡ እንደገና እየታሰሩ እንዲኖሩልን የምንፈልገውስ እስከመቼ ነው? ለእንደዚህ አይነቱ ነገር ዝግጁ ካልሆንን እንዲታሰሩ የምንፈልጋቸው ሰዎች ታስረው ነው የሚቀሩት፡፡ ለታሰሩ ሰዎች አንድ ነገር ማድረግ የማንችል ከሆነና ‹‹እከሌ ለምን ታስሮ አልቀረም›› ለማለት ከሆነ እንቅልፍ የምናጣው፤ ጭካኔአችን የሰው ልጅ ሳይሆን የእንስሳ ጭካኔ ነው፡፡

እኔ በግሌ ለእንደ ተመስገን አይነቱ አክብሮት አለኝ፡፡ ተመስገን ሁለት አመት ታስሮ በይቅርታ ቢፈታና ከዛ በኋላ ‹‹ይቅርታህ ሊነሳ ነው›› የሚል መረጃ ቢደርሰው እና አገር ጥሎ ቢወጣ ‹‹ተመስገን ለምን አልታሰረም›› ብዬ አገር ይያዝልኝ አልልም፡፡

አዲስ መፅሐፍ እየፃፍክ እንደሆነ ሰምተናል፡፡ መቼ እንጠብቀው? ምንስ ነገሮችን አካቷል?

መጽሐፉን ጽፌ የጨረስኩት ባለፈው ነሐሴ ነው፡፡ ነገር ግን ከጠ/ሚኒስትሩ ህልፈት ጋር በተያያዘ ያኔ የነበረው የፖለቲካ ድባብ መጽሀፉን ገበያ ላይ ለማዋል አስቸጋሪ ስለሆነ ከማቆየት ውጪ አማራጭ አልነበረኝም፡፡ አሁን ሁኔታዎች ስለተረጋጉ ከዛ በኋላ የተፈጠሩ አዳዲስ ነገሮችንም ጭምር አካትቼ እንደ አዲስ ለመከለስ ተገድጃለሁ፡፡ አሁን እያለቀ ነው ማለት ይቻላል፡፡ እንደ እግዚአብሄር ፍቃድ በሁለት ወር ውስጥ ይፋ ይሆናል፡፡ ይዘቱን በተመለከተ፡- አጠቃላይ ፕሬሱ ያለፈበትን ውጣ-ውረድ ከራሴ ልምድ ጋር በማዛመድ እቃኘዋለሁ፡፡ ከፕሬስ ነጻነት አንጻር የአቶ መለስ ሚና ምን እንደነበረም ትዝብቴን አሰፍራለሁ፡፡ እንዴት ከአገር እንደወጣሁ፣ የነበሩት ፈታኝ ሁኔታዎች ምን ይመስሉ እንደነበር ለማቅረብ እሞክራለሁ፡፡

ከሀገር ከወጣህ በኋላ የተጻፉ መፅሀፍትን እንዴት አየሃቸው?

እኔ ከተሰደድኩ በኋላ የወጡት መጽሐፎች የአቶ በረከት ስምኦን (በወቅቱ ሪቪው ሰርቼበታለሁ)፤ የኮ/ል መንግስቱ ኃይለማሪያምና የጋዜጠኛ ሲሳይ አጌና ከዚሁ ከዳያስፖራ፤ የተመስገን ደሳለኝና የወሰንሰገድ ገብረኪዳንን አንብቤአቸዋለሁ፡፡ ሌላ ስለ አዲስ አበባ የዝሙት ህይወት እና የመሳሰሉት ነገሮች የሚተርክ መጽሐፍ ደግሞ ‹‹የአውራምባ ታይምስ ሎጎ ተለጥፎበት ወጥቷል›› የሚል ነገር ሰምቻለሁ፤አላየሁትም፡፡ እንደዚህ አይነት ይዘት ባለው መጽሐፍ ላይ የአውራምባን ሎጎ ማስቀመጥ ለምን እንዳስፈለገ እስከ ዛሬ ድረስ አልገባኝም፡፡ እስኪ አጣራለሁ፡፡

እስቲ ደግሞ በቅርቡ ባለህበት አሜሪካ ስለተካሄደው ምርጫ ትንሽ በለን፡፡ ከአገራችን ምርጫ ጋር ስታስተያየው (ማነፃፀሩ አዳጋች ቢሆንም) እንደ ኢትዮጵያዊ ጋዜጠኝነትህ ምን ተሰማህ? በነበርክበት ኦሪዞና ግዛትስ የነበረው የምርጫ ሂደት ምን ይመስላል?

የአሜሪካ ምርጫን በደንብ ተከታትየዋለሁ፡፡ ኦባማ በድጋሚ መመረጡ ብዙ ኢትዮጵያዊያንን አስደስቷል፡፡ ሁሌም የአሜሪካ ምርጫ ስትከታተል የሚያስቀናህ ነገር በእጩዎቹ መካከል ያለው መከባበር ነው፡፡ በተለይ ውጤቱ ከታወቀ በኋላ አንዱ ለሌላው የሚያስተላልፈው የእንኳን ደስ ያለህ መግለጫ ደስ ይላል፡፡ በተለይ ሚዲያዎቹ ያላቸው ነጻነት ይገርምሀል፡፡ ‹‹ሲ ኤን ኤን›› እና ‹‹ፎክስ››ን ጨምሮ በርካታ ሚዲያዎች በራሳቸው መንገድ የተለያዩ መረጃዎችን መሰረት አድርገው ማን እንዳሸነፈ አስቀድመው ይፋ ያደርጋሉ፡፡ እኛ አገር ግን ምርጫ ቦርድ ይፋ ከማድረጉ በፊት እንዲህ አይነቱን የሚዲያ ትንበያ ይፋ ማድረግ አይፈቀድም፡፡ በእርግጥ በአገራችን እንዲህ አይነቱን ትንበያ ለመስራት የቴክኖሎጂ እጥረትና የአቅም ውሱንነት ቢኖርም በጊዜ ሂደት ግን የማይቻልበት ምክንያት የለም፡፡ በአዋጅ መከልከሉ ግን ተገቢ አይደለም፡፡ እኔ ያለሁበት አሪዞና ‹‹ሬድ ስቴት›› ነው፡፡ ማለትም   ሪፐብሊካኖች ናቸው ሁሌ የሚያሸንፉት፡፡ ለምሳሌ ከአራት አመት በፊት ከኦባማ ጋር የቀረቡት ጆ ማኬይን የዚህ አካባቢ ሰው ናቸው፡፡

አዲሱ የአቶ ኃ/ማርያም አስተዳደር በፕሬስ ጉዳዮች ላይ ለውጥ ያመጣል ብለህ ትጠብቃለህ?

እኔ ሁሌም ተስፈኛ ነኝ፡፡ አቶ ኃይለማሪያም እዚህ ለተባበሩት መንግስታት ስብሰባ የመጡ ጊዜ ለእንግሊዝኛው ቪ ኦ ኤ የሰጡትን ቃለምልልስ ሰምቼዋለሁ፡፡ ፓርላማም ላይ የተናገሩት ነገር ተመሳሳይ ነው፡፡ ትንሽ ራሳቸውን መሆን የቻሉ አይመስለኝም፡፡ ፓርላማ ላይ ከእጅ እንቅስቃሴያቸው ጀምሮ አነጋገራቸው፣ በምላሾቻቸው ላይ የሰነዘሯቸው ማስጠንቀቂያዎችና ዘለፋዎች ተገቢ ናቸው ብዬ አላምንም፡፡ እንደዛም ሆኖ ግን ተስፈኛ ነኝ፡፡ ከ38 ዓመት በኋላ እምነት ያለው ሰው ወደ መሪነት ቦታ መምጣቱ ትልቅ ነገር ነው፡፡ እግዚአብሄር ይርዳቸው!

ከኢትዮጵያ በመሰደድህ ምን ያጣኸው ነገር አለ? (የሚቆጭህ፣ የሚናፍቅህ፣ የሚፀፅትህ ነገር አለ?)

ቀደም ብዬ እንደገለጽኩት ስደት ላይ ስትሆን ቁጭት፣ ናፍቆትና ጸጸት ሁሌም ይኖራል፡፡ እኔ ማድረግ የምችለውን ሁሉ አድርጌአለሁ፡፡ ባልወጣና ባልሰደድ ደስ ይለኝ ነበር፡፡ ግን ምን ታረገዋለህ” ከዚህ በፊት እንደገለጽኩት ህይወት መቀጠል አለበት፡፡

የባልደረባህ የጋዜጠኛ ውብሸት ታዬ  ከስዊድን ጋዜጠኞች ጋር በይቅርታ ያለመፈታት ጉዳይን እንዴት አየኸው?

የውብሸት ጉዳይ ብሄራዊ ክብርን የሚፈታተን ነገር ነው፡፡ ከስዊድኖቹ ጋር እንደሚፈታ ሙሉ እምነት ነበረኝ፡፡ እኩል ነው የይቅርታ ሰነዱን የፈረመው፡፡ በዚህ ጉዳይ ላይ ከፕ/ር ኤፍሬም ይስሐቅ ጋር ተነጋግሬአለሁ፡፡ አጥጋቢ ምላሽ አልሰጡኝም እንጂ፡፡ አለም አቀፉ ሚዲያ የሚጮኸው ለስዊድኖቹ ስለነበር የኢትዮጵያ የይቅርታ ህግ ከኢትዮጵያዊያን ይልቅ የውጭ ዜጎችን ተጠቃሚ ሊያደርግ ግድ ነበር፡፡ ትንሽ ግራ የሚያጋባው ውብሸትም ስዊድናዊያኑም ሲታሰሩ አቶ መለስ የነጭ እና የጥቁር ደም እኩል ነው ብለው ነበር በፓርላማ፡፡ ተመርጠው ሲፈቱ ግን እኩል እንዳልሆነ አረጋግጠናል፡፡ ለዚህም ነው ስዊድኖቹ በተፈቱ በማግስቱ ‹‹አድሏዊውና አሳፋሪው ይቅርታ›› ብዬ አርቲክል ለመጻፍ የተገደድኩት፡፡ ለነገሩ ውብሸት የተበደለው ባሰሩት ሰዎች ብቻ አይደለም፡፡ ምክንያቱ ግልጽ ባይሆንልኝም አገር ቤትም ውጭም ያለው ሚዲያ ሆን ብሎ ረስቶታል፡፡ ከታሰረበት ጉዳይ ቀጥተኛ የሆነ ትስስር አላቸው የሚባሉ ዌብሳይቶች እንኳን አንድ ነገር ትንፍሽ ለማለት አልፈቀዱም፡፡ በሌላ በኩል አገር ቤት ያሉ ሚዲያዎችም እንደዛው፡፡ አንድ የሚዲያ ተቋም የራሱን ባልደረባ ብቻ እየመረጠ ማግዘፍና ማጀገን የለበትም፡፡ እስርቤት ስለነበርኩ የሚዲያ ሽፋን ስታገኝና ሳታገኝ የሚሰማህ ብርታት እኩል እንዳልሆነ አውቀዋለሁ፡፡

በቅርቡ የተካፈልክበት ስብሰባ በ (National Endowment for Democracy) የተዘጋጀው ላይ ፅሁፍ አቅርበህ ነበር? ስለስብሰባው ምንነትና ዓላማ ብታብራራልን?

ናሽናል ኢንዶውመንት ፎር ዴሞክራሲ እዚህ ዋሽንግተን ዲሲ የሚገኝ የአሜሪካዊያን አለም አቀፍ የጥናትና ምርምር ተቋም ነው፡፡ የፌሎውሽፕ ፕሮግራምም ይሰጣል፡፡ እንደምታወቀው ወ/ሪት ብርቱካን ለአንድ አመት ገደማ የቆየችው በዚሁ ተቋም ውስጥ ነው፡፡ ይህ ተቋም ባለፈው ጥቅምት “Toward a Democratic Ethiopia” በሚል ርዕስ የኢትዮጵያ ዴሞክራሲ በምን ሁኔታ ላይ ይገኛል የሚል አለምአቀፍ ኮንፈረንስ አካሂዶ ነበር፡፡
ውይይቱ በሦስት ፓነል የተከፋፈለ ነው፡- የመጀመሪያው የፕሬስ ነጻነትና የሲቪክ ድርጅቶች እንቅስቃሴ እንዲሁም ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የወጡት አዋጆች ምን ተጽእኖ አላቸው በሚል ርዕስ የቀረበ ነው፡፡ እኔ (በፕሬስ ነጻነት)፣ ወ/ሮ ማህደር ጳውሎስ (በሲቪክ ድርጅቶች) እንዲሁም የሂዩማን ራይትስ ዎች የዋሺንግተን ዲሲ ተጠሪ ሳራ ሞርጋን (በአዋጆቹ ዙሪያ) ጥናታዊ ጽሁፎቻችንን አቅርበናል፡፡ ቀጥሎ ደግሞ የአሜሪካ መንግስት በኢትዮጵያ ላይ የሚከተለው ፖሊሲ ምን እንደሚመስል አምባሳደር ዴቪድ ሺን እና ፕ/ር ቴሬንስ ሊዮንስ በመጨረሻ ደግሞ የስቴት ዲፓርትመት አሲስታንት ሴክሬታሪ እንዲሁም ሌላው የዩኤስ ኮንግረስ ተወካይ በተከታታይ ጽሁፎቻቸውን አቅርበዋል፡፡ ከኛ ከጽሁፍ አቅራቢዎቹ ውጪ በዚሁ ስብሰባ ላይ አቶ ስዬ አብርሀ፣ አቶ ገብሩ አስራት፣ ዶ/ር መረራ ጉዲና እንዲሁም በዋሺንግተን ዲ.ሲ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ተወካይ የስብሰባው ታዳሚዎች ሆነው ፕሮግራሙን ተከታትለዋል፡፡

አንተ ያቀረብከው ይዘቱ ምን ይመስላል፤ የኤምባሲው ተወካይስ ማን ናቸው? ምንስ አሉ?

እኔ ያቀረብኩት አጠቃላይ ሚዲያው አሁን ያለበትን ሁኔታ የሚያሳይ ነው፡፡ ፕሬዚዳንት ኦባማ ከስብሰባው ከሁለት ሳምንት በፊት በተባበሩት መንግስታት ስብሰባ ላይ ተገኝተው የመናገር ነጻነትን በተመለከተ በጣም ድንቅ የሆነ ንግግር አድርገው ነበር፡፡ እኔ ለንግግሬ መነሻ ያደረኩት ኦባማ ያደረጉትን ንግግር በማስታወስ ነው፡፡ ኦባማ ያሉት ‹‹ሰዎች በሚያራምዱት አመለካከት ምክንያት እስር ቤት መግባት የለባቸውም፡፡ እዚህ አሜሪካ በርካታ ፕሬሶች እኔን ሲያብጠለጥሉ ይውላሉ፡፡ እኔ የአሜሪካ ፕሬዚደንትና የጦር ኃይሎች ጠቅላይ አዛዥ ነኝ ብዬ ግን ምንም የማረገው ነገር የለም፡፡ እንደውም በህገ መንግስታችን የተረጋገጠውን መብት ተግባራዊ በማድረጋቸው ይበልጥ ደስ ነው የሚለኝ›› ነበር ያሉት ኦባማ፡፡ ይህንን መነሻ አድርጌ የእስክንድርን፣ የርዕዮትንና የውብሸትን ሁኔታ በንጽጽር ለማስቀመጥ ሞክሬአለሁ፡፡ ያው አምባሳደር ዴቪድ ሼን ሁሌም …ዴሞክራሲ እኮ ሂደት ነው ምናምን የሚሉት ነገር አለ…እኔ ደግሞ ‹‹አምባሳደር ዴቪድ ሺን፣ እርስዎ በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር እያሉ ስንት ጋዜጦች ነበሩ? አሁንስ ስንት አሉ? ሂደት ማለት ይሄ ነው? ሂደት ማለት እንደዚህ ከሆነ፤ ወደተሳሳተ አቅጣጫ የሚወስድ ሂደት ላይ ነው ያለነው፤ ‹‹እኤአ እዚሁ በዋሺንግተን ዲሲ ተገናኝተን ስናወራ ቢያንስ እኮ እነ አውራምባ ይታተማሉ ብለው ተከራክረውኝ ነበር፤ ዛሬ ግን እነ አውራምባም አይታተሙም፡፡ ይኼ ነው ሂደት? ባለፈው አመት የእርስዎ ዌብሳይት ሳይቀር ኢትዮጵያ ውስጥ እንደተዘጋ ነግረውኝ ነበር” እንዴት ነው ይህንን ማስታረቅ የሚቻለው?›› አልኳቸው፡፡ በጣም የሚያስቀው ነገር ዌብሳይታቸው ኢትዮጵያ ውስጥ ተዘግቶ እንደነበረና ከአቶ ኃይለማሪያም ጋር ተነጋግረው እንዳስከፈቱት ነገሩኝ፡፡ ከኢትዮጵያ ኢምባሲ አቶ ዋሕድ በላይ ናቸው የተገኙት፡፡ አጋጣሚ የእኔ ጽሁፍ ቀርቦ ቤቱ ለጥያቄና መልስ ክፍት ሲሆን አቶ ዋሕድ ተነስተው የኔ ጽሁፍ የደርግ አመለካከት እንደሚንጸባረቅበት ተናገሩ፡፡ እኔ ደግሞ ኢህአዴግ አዲስ አበባ ሲገባ የዘጠኝ አመት ልጅ እንደነበርኩ ተናግሬ በአዳራሹ የነበሩ ታዳሚዎችን ትንሽ ፈገግ አሰኘኋቸው፡፡ በነገራችን ላይ ከዛ በኋላ ከአቶ ዋህድ ጋር አድራሻ ተለዋውጠን ኢንተርቪው ሁሉ እንደሚሰጡኝ ቃል ገብተውልኛል፡፡

አገሬ መጥቼ ተወዳጇን አውራምባ ታይምስ ጋዜጣ ዳግም አሳትማለሁ ብለህ ታስባለህ?

ተስፋ አደርጋለሁ፡፡ ሌላው ቢቀር ቢያንስ ዌብሳይቴን ኢትዮጵያ ሆኜ ብሰራው እንዴት ደስ ይለኛል መሰለህ፡፡ ግን በጣም የሚያሳዝነው ነገር እንደዛ አይነት ሆደ ሰፊነት ኢህአዴግ ጋ የለም፡፡ ይገርምሃል ዌብሳይቱ የተመረቀው ሜይ 05/2012 እንግዶች በተገኙበት በዋሺንግተን ዲ.ሲ ነው፡፡ በተጠቀሰው ቀን ተመርቆ በማግስቱ ግን ኢትዮጵያ ውስጥ ተዘግቷል፡፡ ‹‹አውራምባ ታይምስ በኪሳራ ነው የተዘጋው፤ እኛ ጫና አላሳደርንም›› ያሉት ኃላፊዎች የአውራምባ ዌብሳይትን ግን ከ24 ሰዓታት በላይ ሊታገሱት አልፈቀዱም፡፡ ቢያንስ ይዘቱ ምን ይመስላል? ተብሎ እንኳን ዳሰሳ ለማድረግ አይሞከርም? እና እንዲህ እንዲህ አይነቱን ስመለከት ትንሽ ተስፋዬን ያደበዝዘዋል፡፡ ግን ይሁን እስኪ…………..

Posted By Gheremew Araghaw

Ethiopian high school student in Chicago died after a hit-and-run accident

(NBC Chicago) — An 18-year-old Schaumburg High School student whose lifeless body was found lying in a roadway in the northwest suburb of Chicago early Saturday was being remembered as a beloved friend and athlete by school officials and classmates

Read more :http://www.ethiopianreview.com/forum/viewtopic.php?t=45774&p=259891#p259891

 

posted by Gheremew Araghaw

በደቡብ ክልል ቤንች ማጂ ዞን ከጉራ ፈርዳ የተፈናቀሉ አማራዎች መታሠራቸውና ገሚሶቹም ወደአምቦ መወሰዳቸው ተገለጸ

VOA – በደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል፤ በቤንች ማጂ ዞን ጉራ ፈርዳ ወረዳ የሚኖሩ፤ ከዓመታት በፊት ከአማራ ክልል የሄዱ ሠፋሪ አርሦ አደሮች በአካባቢው ባለሥልጣናት ተገድደው ቀያቸውን ልንዲለቅቁ እየተደረጉ መሆኑን መዘገባችን ይታወሳል።

Read more : http://www.ethiopianreview.com/forum/viewtopic.php?t=45779&p=259943#p259943

posted by Gheremew Araghaw

Finote Democracy weekly News

http://www.finote.org/news/Weekly_Report.pdf

posted by Gheremew Araghaw

“በአገራችን የአሸባሪዎች ድር አለ” ኃ/ማርያም/ የኢትዮጵያ ሙስሊም ቁጥር 35% ነው አሉ

ኢትዮጵያን መምራት ከጀመሩ ሶስት ወር ያስቆጠሩት ጠቅላይ ሚኒስትር ሃይለማርያም ደሳለኝ ኢትዮጵያ በአሸባሪዎች የተከበበች አገር መሆኗን አመለከቱ። ኦብነግ በመገንጠል ስም የፖለቲካ ንግድ የሚያካሂድ ድርጅት እንደሆነ ገለጹ። መንግስታቸው ለሚታማበት ጉዳይ ማስተባበያ አቀረቡ።

ከአልጃዚራ ቴሌቪዥን እንግሊዝኛው ክፍለጊዜ ጋር ቃለ ምልልስ ያካሄዱት አቶ ሃ/ማርያም ስለ አሸባሪዎች የተናገሩት በአገሪቱ የተነሳው የእስልምና ሃይማኖት ጥያቄና ተቃውሞ ስለቀረበበት የአህባሽን አስተምሮ ተከትሎ ከአያያዝ ጉድለት ጉዳዩ ወደ ቀጠናው እንዳይሸጋገር ስጋት ስለመኖሩ ለቀረበላቸው ጥያቄ በሰጡት መልስ ነው።

“ጥያቄው የጥቂቶች ነው” በሚል አቃለው በማቅረብ ማብራሪያቸውን ጀመሩ። መንግስት በሃይማኖት ጉዳይ ጣልቃ እንደማይገባ በማመልከት አብዛኞቹ ሙስሊሞች ጥያቄያቸው የአስተዳደርና የሲስተም መሆኑንን አመላክተው ማንም ያልደፈረውን ጉዳይ አነሱ።ኢትዮጵያ የበርካታ ሃይማኖቶች አገር መሆኗን በመጥቀስም የአኻዝ መረጃ ሰጡ።

በአገሪቱ የክርስቲያኖች ቁጥር ከአጠቃላይ ህዝብ 43 በመቶ፣ ሙስሊሞች 35 በመቶ የተቀሩት ሃይማኖቶች ቀሪውን ቁጥር እንደሚይዙ በተዛዋሪ ተናግረው በሁሉም ሃይማኖቶች ጽንፈኞች መኖራቸውን አስታወቁ። አያይዘውም አገሪቱ በቃጣናው በአሸባሪዎች የተከበበች አገር እንደሆነች አመለከቱ። ይህ አኻዝ አወዛጋቢ ነው ቢባልም The World Factbook የሚባለውና በመላው ዓለም በዋቢነት የሚጠቀሰው የአሜሪካ የስለላ ድርጅት (ሲአይኤ) ድረገጽ በኢትዮጵያ ያሉትን ሃይማኖቶች ቁጥር 43.5በመቶ ኦርቶዶክስ፣ ሙስሊም 33.9በመቶ፣ ፕሮቴስታንት 18.6በመቶ፣ ባህላዊ 2.6በመቶ፣ ካቶሊክ 0.7በመቶ እና ሌሎች 0.7በመቶ በማለት በዝርዝር ያሰፍራል፡፡

ጠያቂዋ እንደ ቢቢሲው የሃርድ ቶክ ጋዜጠኛ ትንታግ ሆና ከማፋጠጥ ይልቅ አቶ ሃይለማርያም መንግስታቸው የሚታማበትን ጉዳይ እንዲያስተባብሉ እድል የሰጠቻቸው በሚመስለው ቃለ ምልልስ አቶ ሃይለማርያም “አሸባሪዎቹ አገር ቤት ድር አላቸው” ሲሉ ማንም አገር እንደሚያደርገው ሁሉ እርሳቸው የሚመሩት መንግስት ከነዚህ ቡድኖች ጋር ግንኙነት ያላቸውን ህግ ፊት እንዳቀረበ ተናግረዋል። በዚህም በሙስሊም ኢትዮጵያውያን የተነሳውን “የመንግስት ጣልቃገብነት” ይቁምና የ“ድምጻችን ይሰማ” ጥያቄ ወደ አሸባሪነት አጠጋግተውታል።

“ማንም ፖለቲከኛም ሆነ የመንግስት ሰው ከህግ በታች ነው” ያሉት አቶ ሃይለማርያም “በህዝብ የተመረጥን እንደመሆናችን የህዝባችንን ደህንነት የመጠበቅ ሃላፊነት አለብን” በማለት ራሳቸው ፈገግ ብለው ጠያቂዋንም አስደምመዋታል። ስለ ኢኮኖሚ እድገት ሲያነሱ በተከታታይ የእጥፍ አኻዝ እድገት መኖሩን አቶ ሃይለማርያም ሲናገሩ “እሱ እውነት ነው” በማለት የምስክር ወረቀት ሰጥታ ወደ ቀጣዩ ጥያቄ የገባችው ጋዜጠኛ የተለያዩ የኢኮኖሚ ተቋማት የኢኮኖሚ ዕድገቱ ከዚህ በታች እንደሆነ የዘገቡትን በንጽጽር በመጥቀስ መስቀለኛ ጥያቄ ሳታቀርብ የቀጠለችው አቶ ሃይለማርያም ነካ ወዳደረጉት የኦጋዴን ነጻ አውጪ ግንባር ጉዳይ ነበር።

የተጀመረው የእርቅ ድርድር የቆመው ህገመንግስቱን ለመቀበል ኦብነግ ፈቃደኛ ሊሆን ባለመቻሉ መሆኑን ያመለከቱት አቶ ሃይለማርያም፣ ህግመንግስት ቅድመ ሁኔታ ባለመሆኑ፣ ኢትዮጵያዊ ለሆኑ ሁሉ ህገመንግስትን ማክበር ግዳጅ በመሆኑ ኦብነግ ይህንን ሊቀበል ባለመፈለጉ ድርድሩ መቋረጡን አመልክተዋል። ኦብነግ የተከፋፈለ እንደሆነ፣ ከተካፋፈሉት መካከል አገር ቤት ገብቶ ህገ መንግስቱን አክብሮ ለመስራት የጠየቀ መኖሩንና መጨረሻው ወደፊት እንደሚታይ ገልጸዋል። ኦብነግ በተመሳሳይ በመጀመሪያ ድርድር የተደረሰበት ስምምነት ያለ አንዳች ቅድመ ሁኔታ ለመነጋገር እንደነበር አስታውቆ የመከላከያ ሚኒስትሩ የመሩት ልዑክ በሁለተኛው ድርድር በቅድሚያ ህገመንግስቱን መቀበል የሚል ቅድመ ሁኔታ በመነሳቱ ድርድሩ መቋረጡን በድርጅቱ ድረገጽ የገለጸውን ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ ማተሙ ይታወሳል

ኦብነግን የሚያነሳው የመገንጠል ጥያቄ በህገመንግስቱ የተረጋገጠ መሆኑን ያወሱት አቶ ሃይለማርያም “በመሬት ላይ ያለው እውነት ሌላ ነው። የፖለቲካ ንግድ ነው የተያዘው” በማለት ተዛልፈዋል። ኦጋዴን ውስጥ መንግስት አደረገ የተባለውን ኢሰብአዊና አስከፊ የማሰቃየት ተግባር አቶ ሃይለማርያም “የአንድ ወገን መረጃ” በማለት ሊቀበሉት አልቻሉም። የቢቢሲ የምርመራ ጋዜጠኛና ሂውማን ራይትስ ዎች ኦጋዴን ውስጥ ከፍተኛ የሰብአዊ መብት መጣሱን ተበዳዮችን በማነጋገር፣ በቪዲዮ የተደገፈ መረጃ በማስደገፍ ማቅረባቸው የሚታወስ ነው። በወቅቱ በህወሃት/ኢህአዴግ የሚመራው የአቶ መለስ አገዛዝ ጉዳዩን በተመሳሳይ አስተባብሎ ነበር።

ስለ መሬት ነጠቃና የመሬት ነጠቃው ለምግብ እጥረት ችግር መንስዔ ስለመሆኑ በማንሳት መልስ እንዲሰጡ እድል ያገኙት አቶ ሃይለማርያም “የመሬት ነጠቃ የለም።ይህ ስህተት ነው” በማለት ነበር ጀመሩት። ከአርሶ አደሮችም ሆነ ከአርብቶ አደሮች ላይ መሬት እንዳልተቀማ፣ ለውጪ ባለሃብቶች የተሰጠው መሬት ሰው የሌለበት ትርፍ የግጦሽ /ሳቫና ላንድ/ እንደሆነ በመግለጽ የጋምቤላና የኦሞ ሸለቆ የቀዬው ነዋሪዎች መፈናቀላቸውን ሸምጥጠው ክደዋል። የምትልመጠመጠዋ ጠያቂ ተጨማሪ ማስረጃ አቅርባ መከራከር ባለመቻሏ ስለድህነት ጥያቄ አንስታ አቶ ሃያለማርያም “በሁሉም አገር ያለ እውነት ነው” የሚል መልስ በመስጠት ተገላግለዋል።

ሁለቱም ምስሎች በጋምቤላ አካባቢ ከሳተላይት የተወሰዱ ናቸው፡፡ ቀያዮቹ ነጥቦችና በቀይ የተከበቡት ቦታዎች በሙሉ በመሬት ነጠቃ ከቀያቸው የተፈናቀሉና ቤታቸው የፈረሰ አባወራዎችን ሲሆን ቢጫዎቹ ደግሞ ተፈናቃዮቹ በግዳጅ የሰፈሩበትን ነው፡፡

አምስት ሚሊዮን ረሃብተኛና በድርቅ የተጎዱ ተመጽዋቾች ስለመኖራቸውና እድገትና በርካቶች ስራ ፍለጋ ወደ የመን ይጎርፋሉ ስለሚባለው አቶ ሃይለማርያም የሚያዝናና መልስ ነው የሰጡት። መልሳቸው አቶ መለስ በዚህ ጉዳይ ላይ ከሚሰጡትና ትተውት ከሄዱት “መጽሐፍ” የተቀዳ ይመስላል፡፡ “ከ25 ሚሊዮን አሁን 90 ሚሊዮን ደርሰናል።” በሚል አምስት ሚሊዮን ርዳታ ፈላጊዎች መኖራቸው ሊገርም የሚችል አለመሆኑን፤ አገር ለቆ ስራ ለመፈለግ ወደ ሌላ አገር መሄድ የፖለቲካ ሳይሆን የኢኮኖሚ ችግር መሆኑን አስታውቀዋል።

ፕሬዚዳንት ኢሳያስን አስመራ ሄደው ለማነጋገር ፈቃደኛ መሆናቸውን የገለጹት አቶ ሃይለማርያም ደሳለኝ በቅርቡ ቀደም ሲል ስምምነት አውርዶ አገር ቤት ከገባው አንድ የኦጋዴን ክንፍ በተጨማሪ ሌሎችም በተመሳሳይ ወደ አገራቸው ለመግባት ጥያቄ ማቅረባቸውን አስታውቀዋል። ይህንን ጉዳይ አስመልክቶ ጎልጉል፡ የድረገጽ ጋዜጣ በድርጅት ሳይሆን በግል ከድርጅት መሪዎች ጋር የውስጥ ለውስጥ ንግግር ከተለያዩ ክፍሎች ጋር በመደረግ ላይ መሆኑን ጠቅሰን መዘገባችን ይታወሳል።

የእስልምናን እምነት ተከታዮችን አስመልክቶ ዜናውን ለማመጣጠን አስተያየት የሚሰጠን አካል ማግኘት አልቻልንም። ሆኖም በዚህና በተመሳሳይ ቀጣይ ስራዎቻችን ላይ የተመጣጠነ ዜና ለማቅረብ ይቻለን ዘንድ፣ በዚህ ዜና ላይ መልስ ወይም መቃወሚያ ካለ፣ በሚታወቅ አድራሻና ማህበር፣ ድርጅት ወይም መልስ ለመስጠት አግባብነት ካላቸው አካላት ቢቀርብልን ለማስተናገድ ፈቃደኛ መሆናችንን ለመግለጽ እንወዳለን።

http://www.goolgule.com/

posted by Gheremew Araghaw

ስለ “አንቀጽ 39” ማንን እናመስግን?

በዋዜማ ዝግጅቶች ሲታጀብ ከርሞ፣ ቅዳሜ የተከበረውን “የብሄር ብሄረሰቦች” ቀንን አስመልክቶ የኢትዮጵያ ሬዲዮና ቴሌቪዥን የተለያዩ አስተያየት ሰጪዎችን በማሳተፍ “አንቀጽ 39 ለዘላለም ይኑር” ብሎናል። እኛም ለዚህ ውለታ ማንን ማመስገን እንዳለብን ለመጠየቅ ተገደድን። ለመልካሙና “የህዝቦች አብሮ የመኖር አለኝታ” ስለሚባለው አንቀጽ 39!

የሶማሌ ብሄር አባል ናቸው። አቶ አብዱላሂ አብዱራሂም ይባላሉ። ዘጠነኛውን “የብሄር ብሄረሰቦች” ቀን አስመልክቶ አስተያየት እንዲሰጡ ተጋብዘው በቴሌቪዥን ብቅ አሉ “… አቅማችሁ ካደገ በኋላ፣ ልጆቻችሁን አስተምራችሁ አቅም ስታዳብሩ ለአንቀጽ 39 ትደርሱበታላችሁ…” እንዳሉዋቸው አቶ መለስን ጠቅሰው ተናገሩ። ትዝታቸው መሆኑ ነው።

ወዲያው አቶ መለስ በወቅቱ እንገነጠላለን ያሉትን የሶማሌ ህዝቦች ሰብስበው ሲናገሩ ታዩ።እንዲህ አሉ “አስራ ዘጠኝ ዓመት የታገልኩበት አላማ እንዳይቀለበስ እፈልጋለሁ። አይቀለበስም ብዬ ቃል ስገባ እናንተን ለመደለል አይደለም። ምክንያቱም ስለመብቱ ምን አልባትም ከናንተ በላይ አስባለሁ። ምንም የሚያሰጋ ነገር የለም። ከልቤ ስለማምንበት ነው” ሌላ አስተያየት ሰጪ ተከተለ። ተከተለች። “አንቀጽ 39 ለዘላለም ይኑር” ተባለ።

“የኢትዮጵያዊነት ፋይዳው በጣም ጥልቅና መሰረታዊ ነው። 80 ሚሊዮን ህዝቦች አንድ ላይ ስናጨበጭብ እንደመጣለን።ተመጋጋቢ ኢኮኖሚ አለን። ለአገራችን ደህንነትም ሃይል ነው” ይህን ምርጥ አባባልም በተመሳሳይ ፕሮግራም የተደመጠው ከቀድሞው ጠ/ሚ አቶ መለስ አንደበት ነው። በዚህ አያበቃም።

“ተበጣጥሰን የምናገኘው ቴክኖሎጂ ተሰባስበን የተሻለ አይደለም። መሰባሰቡ ጠንካራ ነገር አለው። መሰባሰባችን /አንድነታችን/ የመንደር ንፋስ የሚጠራርገውና የሚበጣጥሰው አይደለም።ስሜት አይደለም። ኢትዮጵያዊነት ጠንካራ የሚሆነው ምክንያት ስላለው ነው” አንጀት የሚያርስ አባባል። ወርቅ ንግግር። ከዚያስ?

“ነጻ ኦሮሚያ” የሚሉ ሰልፈኞች ታዩ። መለስ መጡ። አዲስ አበባ እንደገቡ ሰሞን ነው። እንዲህ አሉ “እኛ ጦርነትን በቴሌቪዥን አናውቅም። እኛ ጦርነትን በወሬ አናውቅም። እኛ ጦርነትን በተቃጠሉ ቤቶች፣ በተጨፈጨፈ ህዝብ ነው የምናውቀው። ከእንግዲህ አንዋጋም። በቅቶናል። ሰልችቶናል። ከእንግዲህ አንዋጋም” በማለት የተናገሩትን አሞጋሾችን እየቀላቀለ ኢቲቪ ትውስታ አቃመሰን።

አቶ መለስ አማራ ናቸው፣ አቶ መለስ ሃረሪ ናቸው፤ አቶ መለስ ወላይታ ናቸው። አቶ መለስ ሶማሌ ናቸው። ወዘተ የሚሉ ሰዎች መለስን ባረኩ። የሶማሌ ክልል አስተያየት ሰጪ የአቶ መለስን ፎቶ ጸሃይ ሲመታው አይተው “ፎቶም ቢሆን መለስ እኮ ነው ጥላ አድርጉለት አልኩ” ሲሉ አሁንም ኢቲቪ አስደመጠ። የሃረሪው አስተያየት ሰጪ ከጭቆናው ብዛት ከምድረ ገጽ ሳይጠፉ አቶ መለስ እንደደረሱላቸው መሰከሩ። አቶ ኩማም ኦነግን እየረገሙ አንቀጽ 39 ዋጁ። ታላቅ ገጸ በረከት እንደሆነ ደጋግመው መሰከሩ። ይብቃን!!

“የብሄር ብሄረሰቦች” ቀን ሲከበር የመጻፍ፣ የመናገር፣ የመደራጀት፣ የመቃወም፣ ህዝብ በፈቀደው መንገድ እንዲደራጅ፣ ይህ ካልሆነ እስከመገንጠል መብት አለው የሚል የተጨመቀ ዓላማ እንዳለው በተደጋጋሚ ሰምተናል። ይህንን እየሰማን አማራው መፈናቀሉ ይነገረናል። ለዓመታት ከኖሩበት እየተሰደዱ ልመና ላይ መሆናቸውን ከበዓሉ ጋር የቀጥታ ስርጭት ሆኗል። ህጻናት ለችግር ተጋልጠዋል። አባት ከጎጆው ወጥቶ የቀን ሰራተኛ ለመሆን ተገዷል። ቤተሰብ ተበትኗል። የታሰሩ አሉ። ይህ ሁሉ የሚሆነው “እገሌን ደገፍክ” በሚል የፖለቲካ ቂም እንደሆነ ሰለባዎቹ ሲናገሩ እየሰማን ነው። ለዚህ ታላቅ ብስራት ኢቲቪ ጆሮ የለውም። “ብሄር ብሄረሰቦች” እኩልነትን የተጎናጸፉበትን ክብረ በአል በቀጥታ በማሰራጨት ስራ ተጠምዷል።

ብዙ ሺህ አስረኞች “ኦነግ ናችሁ” ተብለው በአመለካከታቸው ሳቢያ እየተሰቃዩ ነው። ቅንጅን በገንዘብ ደግፋችኋል የተባሉ ከስራና ከንግድ እንዲወጡ እየተደረገ ነው። በቀረጥና በእዳ ስም የተዘረሩና የቁም ሞት የሞቱ አሉ። ጠኔ የሚቆላቸው የበይ ተመልካቾች ችግር ከጓዳ አልፎ አደባባይ ውሏል። ሃሳብን በነጻ መግለጽ የሚቻል መስሏቸውና መብቱ የተፈጥሮም በመሆኑ የተናገሩ፣ የጻፉ፣ የተቹ፣ “አሸባሪ” ተብለው ተከርችመዋል። ስለ መብት መከበርና ስለ እምነት ነጻነት የሚጠይቁ በጋሪ የሚገፋ የክስ ፋይል ተከፍቶባቸው እስር ቤት እየተሰቃዩ ነው። እነዚህ ሁሉ ሰዎች በኢህአዴግ በራሱ ቋንቋ ብሔር የላቸውም? የህዝብ አካል አይደሉም? ይህ መሰረታዊ ችግር እያለ ከበሮ ይደለቃል። ለስርዓቱ የቀለም ማስዋቢያ እንዲሆን ከየብሄረሰብ የተውጣጡ አጊጠው ሲጨፍሩ ይስተዋላል። በብሄርም ደረጃ ወርደን እንነጋገር ከተባለ በተለይ አማራ ክልል ለወገኖቹ መሟገት ሲገባው ባህር ዳር ላይ አስረሽ ምቺው መጨፈሩ ያሳፍራል። ወገኑንና የሚምልለትን ህዝብ የማይሰበስብ ድርጅት!

መራገምና ማውገዝ ሰልችቶናል። የውግዘት መንገድ ለማንም እንደማይበጅ እናውቃለን። ውግዘት ለቀጣዩ ትውልድ መርዝ የመጋት ያህል መራር ውርስ ነው። ግን ምን እናድርግ? የምናመሰግነው አጣን። ማንን እናመስግን? እንዲሁ በቅዠትና በሚያደነቁር ፕሮፓጋንዳ ኖረን እንለፍ?

ዝናውም፣ክብሩም፣ሃብቱም፣ሁሉምያልፋል።ጊዜምከጥላችንይልቅይበራል።ደጎችላገራቸው፣ለቤተሰቦቻቸውናለተተኪውትውልድመልካምነገርአስቀምጠውሲያልፉበበጎሲታወሱይኖራሉ።የክፉታሪክናልምድማጣቀሻከመሆንለአገርናለወገንመልካምስራሰርቶማለፍያኮራልከአዲሲቷኢትዮጵያየጋራንቅናቄድረገጽላይየተወሰደ

 

posted by Gheremew Araghaw

 

ከእሁድ እስከ እሁድ (የሳምንቱ አጫጭር ዜናዎች)

የጉራ ፈርዳ አማሮች መሬታቸው በሃራጅ ተሸጠ

ቪኦኤ ሰለባዎችን በማነጋገር እንደዘገበው የጉራ ፈርዳ ነዋሪ አማሮች መሬታቸውን እንዳያርሱ ከተከለከሉ በኋላ መሬታቸው በሃራጅ እየተሸጠባቸው እንደሆነ ይፋ አድርጓል። መሬታቸውን በህጋዊ መንገድ የግላቸው እንዳደረጉና ግብር እየከፈሉ የሚኖሩት ተበዳዮች ርምጃው የተወሰደባቸው ቅንጅትን በመምረጣቸውና ለመኢአድ መረጃ ትሰጣላችሁ በሚል እንደሆነ ተናግረዋል።

በተደጋጋሚ መታሰራቸውንና በከሰሳቸውን የተናገሩት የጉራ ፈርዳ ነዋሪ ከእስር ከተፈቱ በኋላ “መሬታችሁን የያዛችሁት በህጋዊ መንገድ ነው” በማለት ለመኢአድ መረጃ መስጠታቸው እንደ ጥፋት እንደተወሰደባቸው አመልክተዋል። በ1997 ምርጫ ወቅት በምስጢር የድምጽ መስጫ ክፍል ውስጥ የጤና ባለሙያዎችን በማስቀመጥ ማንን እንደመረጡ መሰለላቸውንም አመልክተዋል። የሚሸጠውን መሬት የወረዳ፣ የቀበሌ፣ የባለስልጣናትና የፖሊስ አባላት በሚስቶቻቸውና በዘመዶቻቸው ሚስት እንደሚገዙት ተናግረዋል። መንግስትም ሆነ የአካባቢው ሃላፊዎች አስተያየት ለመስጠት አልተገኙም። ቀደም ሲል ሰባ ሺህ የሚጠጉ የአማራ ተወላጆች እንዲፈናቀሉ መደረጉ አይዘነጋም።

ሙስሊሞች የህገመንግስት ያለህ እያሉ ነው

መንግሥት ሕገ-መንግሥቱን ጥሶ በሐይማኖታዊ ጉዳያችን ጣልቃ ገብቷል የሚሉት  ሙስሊሞች፣ ሕገ-መንግሥቱ እንዲከበር አበክረዉ እያሳሰቡ ነዉ። የአዲስ አበባ ሙስሊሞች ዓርብ ከጁመዓ ሶላት በኋላ በተለይ የሐይማኖት ነፃነት የተደነገገበት  አንቀፅ ሃያ-ሰባት መጣሱን ቁጥሩን በማሳየት ጭምር አዉግዘዋል።

“ሕገ-መንግሥት የማስከበሩ ሃላፊነት ከአገሪቱ መንግሥት ይልቅ የመብት፣ የነፃነት ተሟጋቾችና ሃላፊነት የሚሰማቸዉ ወጣቶች የመሆኑ እንቆቅልሽ ገሐድ እየወጣ ነዉ” ሲል የዘገበው የጀርመን ሬዲዮ፣ ዞን-ዘጠኝ በሚል መጠሪያ የተደራጁ የድረ-ገፅ ወጣቶች ታዳሚዎች ሕገ-መንግሥቱ የፀደቀበትን አስራ-ስምተኛ ዓመት ምክንያት በማድረግ «ሕገ-መንግሥቱ ይከበር» የሚል ዘመቻ ትናንት ከዓርብ የጸሎት ስነስርዓት በኋላ መጀመራቸውን አስታውቋል። የሙስሊሙ ህብረተሰብ ተቃውሞውን እየገለጸ ያለበት አግባብ ሰላማዊና ከመሆኑ አኳያ ስለ ሰላማዊ ትግልና ‹‹በኢትዮጵያ ሰላማዊ ትግል አይሰራም›› ለሚሉና ለሌሎች ትምህርት የሚሰጥ እንደሆነ እየተገለጸ ነው።

“ጣጣ የለውም” ግርማ ወ/ጊዮርጊስ

ከካው ቦይ ባርኔጣቸው ጋር ምስላቸውና ዜናቸው ሰሞኑን የተሰማው ፕሬዚዳንት ግርማ ወ/ጊዮርጊስ፣ ከቪኦኤ የአማርኛ ሬዲዮ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ አነጋጋሪ ምላሽ ሰጥተዋል። በስደት አሜሪካ የሚገኙትን የኦርቶዶክስ ፓትሪያርክ ከነሙሉ መንበራቸው አገር ቤት እንዲገቡ የሚፈቅድ ደብዳቤ መላካቸውን ተከትሎ አዲሱ አበበ ማረጋገጫ ሲጠይቃቸው አለ ምንም ማቅማማት ነበር ደብዳቤውን እሳቸው እንደጻፉት የተናገሩት፡፡

ደብዳቤው መበተኑን ተከትሎ የእምነቱ ተከታዮች ምርቃትና ምስጋና ውሎ ሳያድር አዲሱ አበበ ተጨማሪ ዘገባውን በድምጽ ጥራት አሳቦ አስከተለ። ይህኔ ነበር “ውሳኔው የግሌ ነው። የመንግስት አይደለም። አንስቼዋለሁ” በማለት እንደ አራዳ ልጆች “ጣጣ የለውም” አይነት ምላሽ ነው የሰጡት። መቶ አለቃ ግርማ ተጠባባቂው አቡነ ህዝቅኤል እንደተቆጧቸው ገልጸው ሃሳባቸውን መቀየራቸውን ሲያስታውቁ በስህተት “እገሌ ነው የተቆጣው” አለማለታቸው ድምጻቸው ከመቆራረጡ በስተቀር የሶፍትዌር ችግር እንደሌለባቸው ያረጋገጠ ሆኗል። ፕሬዚዳንት ግርማ ሃሳባቸውን ለመቀየራቸው በተደጋጋሚ ሲጠየቁ አቃለውና ተረጋግተው “ሃሳቤን ትቼዋለሁ፣ የመንግስት ውሳኔ አይደለም፣ በችኮላ የተደረገ ነው፣ የሄዱት ቢመለሱ ምንም አይደለም ከሚል ነው። አቡነ ናትናኤል ጣልቃ አትገባ አሉኝ፣ እኔ እንደዚህ ከኋላው ጣጣ ያለው አልመሰለኝም” በማለት ሌላ የፖለቲካ ዝርዝር ሳይቀላቅሉ ጨርሰዋል።

የመለስ ውርስ (ሌጋሲ)፡ ወደብ አልባነታችን!!

በጅቡቲ ወደብ ላይ ያለውን ክምችት በመቀነስ የኪራይ ወጪ ለመቀነስ ታስቦ የተገነባው የሰመራ ደረቅ ወደብ ግንባታ በርቀቱ ሳቢያ ተጠቃሚ ማጣቱ ተሰምቷል።ስራውን ከሚመራው ክፍል ያገኘውን መረጃ ጠቅሶ ሸገር ኤፍ ኤም እንደዘገበው የሰመራ ወደብ የተቋቋመለትን ዓላማ አላሳክም። ዘገባው ዳር ዳር ቢልም የሰማራ ደረቅ ወደብ ሙሉ በሙሉ ለተዋለለት ውሎ ለጅቡቲ የሚከፈለውን ወጪ መቀነስ አላስቻለም።

በ650 ሚሊዮን ብር ወጪ፣ በ14 ሄክታር ሞጆ ላይ የሚገነባው ደረቅ ወደብ ግንባታ ከቅርበቱ አንጻር ባስቸኳይ ለማጠናቀቅና ለወደብ ኪራይ የሚወጣውን ወጪ ለመቀነስ ትኩረት መሰጠቱን የሚመለከታቸው ሃላፊዎች ለሸገር ተናግረዋል። የሞጆ ደረቅ ወደብ ግንባታ ከተጀመረ አራት ዓመት አስቆጥሯል። ወደቧን አስረክባ በየበረሃው የምትዳክረዋ አገራችን ለዚህ ችግር የተዳረገችው በራስዋ መሪዎች መሆኑ ከችግሩ በላይ የሚያቃጥል የታሪክና የዘመን ሁሉ በሽታዋ መሆኑ ነው። ምስጋና ለህወሓትና መለስ!!

ብሄራዊ ባንክ በወርቅ ስም ተጭበረበረ

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ በሚያካሂደው የወርቅ ግብይት ከአንድ የወርቅ አቅራቢ ወርቅ ነው ተብሎ ቁርጥራጭ ብረቶችና እንጨቶች በሳጥን እየታሸጉ ይደርሱታል፡፡ለራሱ ከፍያለው ኡመታ የሚል ሀሰተኛ ስም፣ መታወቂያና የንግድ ፈቃድ በማወጣት ሲንቀሳቀስ የነበረው ግለሰብ ፥ ከባንኩ ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች ጋር በነበረው የጥቅም ግንኙነት 29 ጊዜ ወርቅ ነው እያለ ይህን ባእድ ነገር ሲያቀርብ ቆይቷል። በባንኩ የስራ ሃላፊዎች የሻኪሶ ቅርንጫፍ ጥፍጥፍ ወርቅ ተረክበናል የሚል ማረጋገጫ ተሰጥቶት ክፍያው እንዲፈጸም ተደርጎ ፥ ከ95 ሚሊዮን ብር በላይ የሆነ ገንዘብ በመቀበል ለግል ጥቅሙ ማዋሉን የዘገበው ፋና ብሮድካስቲንግ ነው።

ጉዳዩን ሲከታተል የቆየው የፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት 15ኛ ወንጀል ችሎት በዚህ ተከሳሽ ላይ ከዚህ ቀደም የጥፋተኝነት ብይን ያሳለፈ ሲሆን ባሳለፍነው ሳምንት በዋለው ችሎት ደግሞ ፥ በወቅቱ የባንኩ የውጭ ምንዛሬ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር የነበሩትን አቶ ሰይፈ ደስታን ጨምሮ በ5 የባንኩ ሀላፊዎች ላይ የጥፋተኝነት ብይን ቢሰጥም ፣ፍርድ ቤቱ 3ኛ ተከሳሽ የነበሩትን አቶ ዋሱ አደም አሊን የቀረበባቸውን ክስ በሚገባ ተከላክለዋል በማለት በነጻ አሰናበቷቸዋል፡፡ ለመጨረሻ ውሳኔም ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡ ብሄራዊ ባንክ ወርቅ ገዛሁ እያለ ባዕድ ነገር በመግዛት በተደጋጋሚ ከፍተኛ ገንዘብ መጭበርበሩ የሚታወስ ነው።

አላሙዲ የተለመደው ማስጠንቀቂያ ደረሳቸው

የሚድሮክ እህት ኩባንያ የሆነው ሁዳ ሪል ስቴት ከ15 ዓመታት በፊት መሀል ፒያሳ ላይ ወስዶ ያጠረውን መሬት ግንባታ የማይጀምርበትና በፍጥነት ገንብቶ የማያጠናቅቅ ከሆነ እንደሚነጠቁ አስጠነቀቀ። ቦታውን ወስዶ ለሌላ ልማት እንደሚያውለው ሪፖርተር የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመሬት ልማትና ማኔጅመንት ቢሮ ኃላፊ ጠቅሶ ዘግቧል።

በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የመሬት ልማትና ማኔጅመንት ቢሮ ኃላፊ አቶ ጌታቸው አምባዬ  እንዳስታወቁት፣ ሁዳ ሪል ስቴት ፒያሳ ላይ አጥሮ ያስቀመጠው መሬት ላይ ጅምር ሥራዎች አሉ፡፡ በሚፈለገው መንገድና ፍጥነት ግን አልሄደም፡፡ እስካሁን ለመዘግየቱ የራሱ ምክንያቶች ይኖሩታል፡፡ ምክንያቶቹ እንደተጠበቁ ሆነው መዘግየቱ ሁሉንም ያስማማል፡፡ በአሁኑ ወቅት ግን ለመጨረሻ ጊዜ ወደ ግንባታ መግባት አለበት፡፡ ካልሆነ መሬቱን እንደሚረከቡ አስጠንቅቀዋል። አስተዳደሩ ላለፉት አስራ ሁለት ዓመታት ከማስጠንቀቅ የዘለለ ርምጃ መውሰድ አለመቻሉ ትዝብት ላይ ጥሎታል። ሼኽ መሀመድ አላሙዲ ቦታውን የተረከቡት ከሊዝ ክፍያ ነጻ መሆኑ የሚታወቅ ነው። (በተዛማጅ ጉዳይ ላይ ጎልጉል፡ የድረገጽ ጋዜጣ ሰሞኑን አጠር ያለ ዘገባ ያቀርባል)

ዘራፊዎቹ ፖሊሶች ተፈረደባቸው

የአዲስ አበባ ፖሊስ አባል የሆኑ ሶስት ታጣቂዎች በመሳሪያ በማስፈረራት ወንጀል የሌለበትን ሰው ቦሌ ካራማራ ሆቴል አጠገብ በማስቆም በህግ እንደሚፈለግ ከገለጹ በኋላ ካቴና በማውጣት እጁን ያስሩታል። ተከሳሽ ኮንስታብል አዲስ ደሳለኝ እና እንደሻው መላኩ ወንጀሉን ካልተያዘው ተባባሪያቸው አቶ ገመችስ ጋር በመሆን ያከናወኑት ጥቅምት 15, 2005 ዓ.ም ረፋድ ላይ ነው። ሸገር ኤፍ ኤም ራዲዮ እንዳስታወቀው ተበዳይ አቶ መሃመድ ዑመርን የሰራኸው ህገ ወጥ ስራ ስላለ ለጥያቄ እንፈልግሃለን ብለው በማስፈራራት በዕለቱ 20 ሺህ ብር ካላመጣ እንደሚገሉት ያስፈራሩታል። ለጊዜው የያዘውን 8100 ብር እና የኪስ ቦርሳውን ይረከቡታል።

የቀረውን ብር ለማግኘትም ለጓደኛው እንዲደውል በማስገደድና በማስደወል 10 ሺህ ብር ተጨማሪ ይወስዳሉ። የተረፈውን ብር ከ2 ቀን በኋላ ለመቀበል ቦሌ ሚካኤል አካባቢ ይቀጣጠሩና ስፍራው ይደርሳሉ። በውላቸው መሰረት ሃያ ሺህ ለመሙላት የጎደለውን 1900 ብር ሲቀበሉ እጅ ከፍንጅ በመያዛቸው የክስ ሂደቱ በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ቦሌ ምድብ 2ኛ የወንጀል ችሎት ሲታይ ቆይቶ ፥  እያንዳንዳቸው በ4 አመት ጽኑ እስራትና 7 ሺህ ብር እንዲቀጡ ተደርጓል። በባንክ የተገኘው አስራ አራት ሺህ ብር ለተበዳይ እንዲመለስ ተደርጓል። ገመቺስ የተባለው ተጠርጣሪ ፖሊስ አልተያዘም። ቅጣቱም ተመጣጣኝ አይደለም ከመባል አልፎ በአገሪቱ ውስጥ ሕግ ማስከበር የሚገባቸው ሥልጣናቸውን ከለላ በማድረግ የሚያካሂዱትን ግልጽ ዘረፋ በጨረፍታ የሚያሳይ ነው ተብሏል።

http://www.goolgule.com

posted by Gheremew Araghaw

አገራችንን እያቃጠለ ያለዉን እሳት ተረባርበን እናጥፋ!

ኢሳ አብድሰመድ

በሀገር ውስጥም ሆነ በወጪው የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን  አንድነትን ከማሰብ ይልቅ ግላዊ ጥቅምን ማሳደድን የተሻለ ምርጫ አድርገው ይዘውታል በሃገራችን ውስጥ ያሉ ፓርቲዎች  የአቅማቸውን ያህል ቢንቀሳቅሱም በሀገራቸው ውስጥ የሚደረግባቸው ተጽእኖ   አንደሁለተኛ ዜጋ መታየታችው  ሀገር ያወቀው ጸሃይ  የሞቀው ጉዳይ ነው::

አንዳንዶች ደግሞ የፓርቲዎችን  ስም  ተገን  በማድረግ  እንደ አስመጭና ላኪ የንግድ ስራውን አጧጡፈውታል  በርግጥ  የፓርቲዎችን  መኖር  መጥላቴ ወይም  መንቀፌ ሳይሆን በሀገር  ውስጥም  ይሁን በውጭ ያሉ ፓርቲዎች  እንደገዢው የወያኔ  ቡድን  ያመጣው  የዘር  ክፍፍል በሽታ ወይንም  ቫይረስ  ተጠናውቷቸዋል  በመሆኑም በዘር ተደራጅቶ  መጉአዝን አማራጭ አድረገው  ሲከተሉ  ይስተዋላሉ ። ከሀገራዊ ፓርቲነት ይልቅ  በጎሳና በዘር ላይ ማተኮርን ይመርጣሉ። ይህም  ደሞ ከአንድነት ይልቅ መበታተንን  የሚያስከትል  በሽታ ነው ።

በጋራ መስራት በፓርትዎቻችን ዘንድ  ተራራን የመናድ ያክል ከባድ ሆኖባቸዋል ። ፓርቲዎች  የጋራ  አቁዓም  ኖሯቸው  ለሀገር ሉዓላዊነት በአንድ ላይ የመስራት ፍላጎታቸውን ወደጎን ትተውታል። የተዋቀሩበትንም  ክቡር አላማ  የዘነጉት ይመስላል።

ኢትዮጵያውያን ለዘመናት አንድ አድረጎ  ያኖረንና  ያጣመረን  የነፃነት አርማችን ሰንደቃችን መሆኑ ይታወቃል :: ሕብረ ብሂራዊነት በማይዋጥላቸው አና ጠባብ አመለካከትን  በሚያራምዱ ጥቂት ሆዳሞች  ዘንድ ግን አንድነት ትርጉሙን  እንዲስት: ህብረት እና  እድገት የሰለጠነባትን  ሀገር  የመገንባት ሕልም ወደ  ጎን ችላ እየተባለ ግላዊ ጥቅም ከሀገር ጥቅም አንዲቀድም አየተደረገ  ያለበት ግዜ ላይ  ደርሰናል ::

ሕዝብ ሰላማዊ የሆነ ዲሞክራሲያዊ  ስርዓት ሰፍኖ ማየት የማንኛውም  ሰባዊ እና ዲሞክራሲያዊ  መብቶቹ  ተከብረው እና ሀገር ባለፀጋ  ሆና ማየት የምን ጊዜም ፍላጎቱ ቢሆንም ሀገራችንን  እንደመዥገር  ተጣብቀው አየመጠመጡ  ባሉት የሰሜን  ወንበዲዎች ዘንድ ጆሮ ዳባ ልበስ አየተባለ እዚህ ደርሰናል’

ኢትዮጵያ  ዘመን ተሻጋሪ የሰንደቅ አላማ ታሪክ ካላቸው ሃገራት መካከል አንዷ ናት ፤ የኢትዮጵያ ሰንደቅ አላማ እስከ 1890 ዎቹ  ሁለተኛ  አጋማሽ  ድረስ በቀለማትም  አንድ ወጥ አልነበረም ፤ አረንጓዴ፣ ቢጫና ቀይ ቀለማት ያሉት ሰንደቅ አላማ ቀለማት ወጥነት ባለው በተያያዙ አራት ማእዘናት በጥቅም ላይ የዋሉት በ1890 ዎቹ  መጨረሻ ነው ፤

በሃገራችን ለመጀመሪያ ጊዜ ለሰንደቅ አላማ ልዩ ትርጓሜና ስርፀት የተሰጠው በ1898 እንደሆነ ይነገራል ፤ ቢጫ የብርሃን፣ ቀይ የመስዋዕትነትና አረንጓዴ የተስፋ ምልክት ተደርጐ ይወሰዳል፡፡ ከዚህ በኋላ ሰንደቅ አላማችን አንድ ጊዜ መንፈሳዊ ሌላ ጊዜ ፖለቲካዊ ትርጓሜ እየታከለበት ዘመን ተሻግሯል ፤ እኛ ኢትዮጵያውያን በሰንደቅ አላማችን ስም በጐም ሆነ መጥፎ ተግባራት በተፈፀሙባቸው ዘመነ መንግስታት ጭምር ለሰንደቅ አላማችን ያለን ፍቅርና ክብር እጅግ ጥልቅ ነው ፤  ምንም  እንኳን የወያኔ መንግስት ባንድራ ጨርቅ ነው ቢልም  ጥንታውያን ጀግኖች ወላጆቻችን ሰንደቅ አላማችንን ይዘው አስደናቂ ትግልና ውጊያ በማካሄድ ከባዕዳውያን ቀጥተኛ ተፅዕኖ ነፃ የሆነች ሃገር አስረክበውናል ፤ በአንዲት ባንዲራቸው ጥላ ስር በመሆን ወራሪውን ሃይል በእግዚአብሔር ረዳትነትና እና በታማኝ አርበኞች ጀግንነት ከቀኝ ግዛት ነጻ የሆነች ሀገር አቆይተውልናል ፡፡

ኢትዮጵያውያን ለአያሌ ዘመናት ብሔራዊ ክብራችንን ባዋረደና እንደ ህዝብ አንገታችንን ባስደፋን አስከፊ የድህነት ማቅ ውስጥ ኖረናል ፡፡ አሁን ሰንደቅ አላማችን የጭቆናም የጭፍጨፋ አርማ አይደለም። የሰንደቅ አላማችን አረንጓዴ፣ ቢጫና ቀይ ቀለማት እንደ ዱሮው ሁሉ የልምላሜ የተስፋና ለነፃነት የሚከፈል መስዋዕትነት ምልክቶቻችን ናቸው ። እራሱን መንግስት አድርጎ በመሰየም ኢትዮጵያንና ህዝቧን እያማረረ የሚገኘው የወያኔ ቡድን በግዴለሽነት ሀገራችን ወደ ድህነት: ሁከት: እና ብጥብጥ  ዜጎችን በማፈን  በማፈናቀል  አና በማሳደድ ተግባሩ የሚታወቅው የአቶ መለስ የአገዛዝ ስርዓት ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ሞት በኋላ  የፖሊሲ  ለውጥ  ሳያደርግ  እየመራት ይገኛል፤ ዜጎቿ እውነት እና ፍትህ ናፍቋቸው የፍትህ ያለህ እያሉ ቀን ከሌሊት እየጮሁ ይገኛሉ፤ ንፁሃን ዜጎች በወያኔ ሴራ እየተቀጠፉ ናቸው፤ እጅግ ሰብዓዊነት በሌለው ሁኔታ ዜጎች እየተደበደቡ እና እየተገደሉ ይገኛሉ፤ ስለመብት መጠየቅና ሰው ሁኖ መገኘት እንደ አሸባሪነት ከመታየቱም አልፎ ለመብታችን በመቆማችን  ብቻ አሸባሪዎች እየተባልን እንጠራለን፤ የኢትዮጵያ  ህልውና  ቀን በቀን እያሽቆለቆለ አስጊ ደረጃ ላይ መድረሱን እየተመለከትነው ነው:: እኛ ኢትዮጵያውያን እንደዜጋ ይሄን አሰቃቂ በደል ቁጭ ብለን ማየት አይገባንም፤ ሀገራችን የአምባገነኖች መፍንጫ  ሁና  ንፁሃን ዜጎቿ ስቃይና መከራ ሲፈራረቅባቸው ማየት ህመም ነው፤ ሀገራችን ክብሯን  ጠብቃ  መኖር አለባት እንጂ የአምባገነኖች  መነሀሪያ መሆኗ ሊያበቃ  ይገባል፡፡ ለአንዴና ለመጨረሻ ግዜ  አገራችን እያቃጠለ ያለዉን እሳት ተረባርበን እናጥፋ! ይህ እሳት በአስቸኳይ ካልጠፋ ወደፊት አገራችን ብለን የምንመካባት ኢትዮጵያ አትኖርም::  በዘር በሃይማኖት በቋንቋ ሳንከፋፈል እጅ ለእጅ ተያይዘን በመነሳት አገራችን ኢትዮጵያን የአምባ ገነን አመራርን  ከስሩ ነቅሎ ለማስወገድ  የተባበረ  ኢትዮጵያዊ  ክንዳችንን በአንድ ላይ ልናውለው  ይገባል::   የጋራ ሃላፊነትን ለመወጣት ለሚተሳሳቡና ለጋራ ጥቅሞቻቸው መከበር ውጤት ለሚያስመዘግቡ እንጂ ለጥቂት ግለኛ ሆዳሞች እንዳልሆነ እስከ መጨረሻው በመፅናት ታሪክ እንሰራለን::  ስለዚህ አገራችንን እያቃጠለ ያለዉን እሳት ተረባርበን እናጥፋ! ይህ እሳት በአስቸኳይ ካልጠፋ ወደፊት አገራችን ብለን የምንመካባት ኢትዮጵያ አትኖርም:: በዘር በሃይማኖት በቋንቋ ሳንከፋፈል እጅ ለእጅ ተያይዘን በመነሳት አገራችን እንታደግ ::

ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር

 

posted by Gheremew Araghaw

የዕርቀ ሰላም ውይይቱ ተጠናቋል (ደጀ ሰላም)

የዕርቀ ሰላም ውይይቱ ተጠናቋል – ዛሬ መግለጫ ይሰጣል፤ በአቡነ መርቆርዮስ ጉዳይ ተጨባጭ ስምምነት ላይ የተደረሰ አይመስልም

(ደጀ ሰላም ኅዳር 30/2005 ዓ.ም፤ ዲሴምበር 9/2012/ READ THIS NEWS IN PDF)፦ በአሜሪካዋ የቴክሳስ ግዛት ዳላስ ከተማ ከኅዳር 26/2005 ዓ.ም ጀምሮ ሲካሄድ የሰነበተው የአባቶች ዕርቀ ሰላም ውይይት በመልካም ሁናቴ በመካሔድ ላይ ቆይቶ ቅዳሜ የተጠናቀቀ ሲሆን ዛሬ እሑድ መግለጫ በመስጠት ይፈጸማል ተብሎ ይጠበቃል።

በአጀንዳዎቹ ላይ በመግባባትና በመከባበር ውይይቱን ያደረገው ጉባኤው ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆርዮስ ከሥልጣናቸው እንዴት ሊወርዱ እንደቻሉ በአገር ውስጥም በውጪው የሚገኙት አበው ልዑካን የታሪክ ምስክርነታቸውን ከሰጡ በኋላ የብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆርዮስ ወደ ኢትዮጵያ መመለስ አስመልክቶ ረቡዕ ዕለት ሰፊ ውይይት መደረጉንና ሳይጠቃለል በይደር መገታቱን መዘገባችን ይታወሳል።

በአገር ውስጥም ሆነ በውጪ ባሉ አባቶች እና ምእመናን ዘንድ በጉጉት የሚጠበቀው የአራተኛው ፓትርያርክ የብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆርዮስ ጉዳይ ዋነኛው የመነጋገሪያ አጀንዳ በሆነበት በዚህ ጉባዔ ከሁለቱም ወገን የተለያየ ሐሳብ ከመቅረቡ አንጻር ለጊዜው ከስምምነት ላይ የተደረሰበት አይመስልም።

ከአገር ቤት የመጣው ልዑክ “ቅዱስነታቸው በመረጡት ቦታ በጸሎት ተወስነው ይቀመጡ” ሲሉ በውጪ የሚገኙት አበው ደግሞ “ከነሙሉ ማዕረጋቸው ወደ መንበራቸው ይመለሱ” የሚለውን ሐሳብ አቅርበዋል። በሁለቱም በኩል ሐሳቡ ዕልባት ሳይሰጠው ቀርቷል። ጉባዔው ዛሬ መግለጫውን ሲሰጥ በዚህ ርዕሰ ጉዳይ ዙሪያ በሌላ ጊዜ ድጋሚ ተገናኝቶ ይወያይ እንደሆነ የደረሰበትን የውሳኔ ሐሳብ ያሳውቃል ተብሎ ይጠበቃል።

ስለ አቡነ መርቆርዮስ መመለስ ግልጽ ደብዳቤ የጻፉትን የፕሬዚዳንት ግርማ ወ/ጊዮርጊስን ሐሳብ አስመልክተው ለአሜሪካ ድምጽ ራዲዮ ጣቢያ ቃለ ምልልስ የሰጡት ዐቃቤ መንበረ ፓትርያርክ አቡነ ናትናኤል ከትናንት በስቲያ አርብ “ፓትርያርኩ በተወሰነላቸው ቦታ እንዲቀመጡና ለአገራቸው አፈር እንዲበቁ” እንጂ ሌላ ነገር እንደማይጠበቅና እንደማይወሰን መናገራቸው የዕርቅና የሰላም ውይይቱ ሳይጀመር የተፈጸመ አስመስሎት ሰንብቷል። ለሰላም ውይይት ምንም ዓይነት በር መዘጋት እንደሌለበት ከማመን አንጻር አሁንም ውይይቱ እንዲቀጥል የሁሉም ተስፋ ነው። የመግለጫውን ሙሉ ሐሳብና ዝርዝር ጉዳዩን እንደደረሰልን እናቀርባለን።

 

http://ethioforum.org

 

posted Gheremew Araghaw

ጠ/ሚ/ር ሃ/ማሪያም ደሳለኝ የጦር ሃይሎች ጠ/አዛዥነቱ ስልጣን አልተቀበሉም።ፕ/ት ነጋሶ ከስልጣን ለመልቀቅ የወሰኑበት አንዱ ምክንያት

The theory and practice of Meles Zenaw

By Alex de Waal|African Affairs 

 

In the months following his death on 20 August, Ethiopia’s Prime Minister Meles Zenawi has been eulogized and demonized in equal measure. But his policies, and the transformational paradigm on which they were based, have rarely been elucidated. While alive, Meles was equally indifferent to praise and blame. To those who acclaimed Ethiopia’s remarkable economic growth, he would ask, do they understand that his policies completely contradicted the neo-liberal Washington Consensus? To those who condemned his measures against the political opposition and civil society organizations, he demanded to know how they would define democracy and seek a feasible path to it, in a political economy dominated by patronage and rent seeking?

Read more: http://www.gulelepost.com/2012/12/09/the-theory-and-practice-of-meles-zenawi/

posted by Gheremew Araghaw

በቅርቡ በሁለት ልጆቿ አባት በ18 ጥይት ተደብድባ የሞተቸው ወ/ሮ ፍሬህይወት ታደሰ በወቅቱ ከፍሬህይወት ጋር አብረው በመኪና ውስጥ የነበሩትና በሶስት ጥይት የቆሰሉት እናቷ ወ/ሮ ተናኘ ሀ/ማርያም ከቁምነገር መፅሄት ጋር ያደረጉት ቃለመጠይቅ

fere

ቁምነገር፡- ፍሬህይወት በትዳር የነበራት ህይወት
ምን ይመስል ነበር?

ወ/ሮ ተናኜ፡- ፍሬህይወት በትዳር በሰላም
የኖረችው ለአንድ ዓመት ብቻ ነው፡፡ ቀሪው 4
ዓመት በመከራ ውስጥ ነበር የኖረችው ለማለት
እችላለሁ፡፡ ነፍሷ አልወጣም እንጂ በጭንቅ ውስጥ
ነበረች ያለችው፡፡
ቁምነገር፡- እንዴት?
ወ/ሮ ተናኜ፡- እየደበደባት፣ ፀጉሯን እየነጨ፣
በረኪና ጠጪ እያለ ነበር የኖረችው፡፡ ለምሳሌ አንድ
ጊዜ የዛሬ ሁለት ዓመት ገደማ የፍሬህይወት ታናሽ
ወንድም ማታ ቤታቸው ውስጥ ነበር፡፡ ታላቅ ወንድሜ
የሚለው ሰውም ሊጠይቀኝ መጥቷል ይል ነበር፡፡ ከዛ
ሌሊት ተነስቶ ሲደበድባት ወንድሟ እኛ ጋር ደውሎ
ድረሱላት ይለናል፡፡ የለበስነውን ነገር አናውቅም፡
፡ በለሊት ከአባቷ ጋር ተያይዘን ኮንትራት ታክሲ
ይዘን እንሄዳለን፡፡ ግን እንዴት ብለን በር አስከፍተን
እንግባ፡፡ በር ላይ ቆመን ሳለን ወንድም የተባለው
ሰው መጣ፡፡ ከዚያ ‹‹ ወንድሜ ምን ድን ነው ችግሩ
ጥፋቱስ የማን ነው?›› ብዬ ስጠይቀው ‹‹ልጅዎ ጋር
ምንም ችግር የለም፤ ጥፋቱ ሁሉ የሱ ነው፡፡ የሚችሉ
ከሆነ ልጅዎን ያድኑ›› ነበር ያለኝ፡፡ ከዛ ተያይዘን ወደ
ቤት ውስጥ ስንገባ የሷ ፊት ቀልቶ ተቀምጣለች፡፡ እሱ
ውስኪ በጠርሙስ ይዞ ተቀምጧል፤ ምንድን ነው
ልጄ? ስለው‹‹ ምን ልትሰሩ መጣችሁ›› ነበር ያለን፡፡
ለምንድን ነው እንደዚህ የምትለው ስለው ወደ ሌላ
ክፍል ገባ ትንሽ ቆይቶ ተመልሶ መጣ፡፡ ከዛ መዛት
ጀመረ፡፡ ሁኔታው አላምር ሲለኝ ይዘናት እንሂድ
አልኩት፡፡ ግን በሌሊት መጥተው ሚስቴን ይዘውብኝ
ሄዱ ብሎ ለወሬ እንዲመቸው ሊያደርግ ይችላል ብዬ
የለም ጠዋት ሲነጋ ችግሩን እንነጋገራለን ብዬ እዚሁ
ነው እኔ የማድረው ብዬ መኝታ ቤት አስገብቻት
በሩን ቆልፈን ተኛን፡፡ እሱ እዛው ውስኪውን ይዞ
ሳሎን ተኝቶ 11 ሰዓት ሲሆን ተነስቶ ወጣ፡፡ እንደዚህ
እንደዚህ ዓይነት ነገሮችን እየፈፀመባት ነበር ዓመታት
ያለፉት፡፡
ቁምነገር፡- ችግሮች ሲፈጠሩ በሽማግሌዎች በኩል
ለመፍታት አልተሞከረም?

ወ/ሮ ተናኜ፡- የቀረ ነገር እኮ የለም፤ የቅርብ
ሚዜዎች ሳይቀሩ የተከበሩ ትላልቅ የቤተክርስቲያን
ሰዎች ሳይቀሩ ጉዳዩን ያላዩ ሰዎች የሉም፡፡ ሰውየው
ምላሱ አይቻልም፤ የማይለው ነገር የለም፡፡ ዛሬ ተፈታ
የተባለ ችግር ነገ እንደገና ይመጣል፤ ሰው ከቁብ
የሚቆጥር ሰው አይደለም፤ በየጊዜው ይጠጣል፣
ያጨሳል፤ ሌላው ቀርቶ ያድራል ያልቻለችው ነገር
አልነበረም ፡፡
ቁምነገር፡- የቅርብ በሚባል በሱ ዘመዶች በኩልስ
ችግሩን ለመፍታት አልሞከራችሁም?

ወ/ሮ ተናኜ፡- ምን ዘመድ አለው፤ እኛ የትስ
እናውቃቸዋለን? ከሠርጉ በኋላ ለመልስም ሆነ
ለቅልቅል ጊዜ ይዟቸው የሚመጣው ጓደኞቹንና
ሚዜዎቹን ነው፡፡ መሰረቱንም ቤተሰቡንም
አስተዋውቆን አያውቀም፡፡ ያው የሴት ልጅ ነገር
ትውውቃቸው በውጪ ነው፡፡ ዘመዶችህ ቤተሰቦችህ
እነማን ናቸው የሚል ጥያቄ አላቀረበችለትም፡፡
በውጪ ተዋውቀው ሽማግሌ ተላከ አባቷ አልቀበልም
አለ ፡፡
ቁምነገር፡-ለምን?
ወ/ሮ ተናኜ ፡- የመጡት ሰዎች የራሱ ስራ
አለው፣ ትልቅ ሰው ነው፣ ቤቱም እዚህ ራስ አምባ
ሆቴል አጠገብ ነው ምናምን አሉ፡፡ አባቷ ግን ልጄን
አልሰጥም አለ፡፡ ምክንያቱም ፍሬህይወት ገና ልጅ
ነች ለትዳር ሳይሆን ለትምህርቷ ነው ቅድሚያ
መስጠት ያለባት፤ ካገባች ትወልዳለች፣ ከወለደች
ደግሞ ትምህርቷን ለመማር አትችልም፤ ትምህርቷን
ትጨርስና ይደርሳል ነው ያለው፡፡ ሽማግሌዎች
ለ12 ጊዜ ያህል ቀጠሮ ስጡን እያሉ ተመላልሰዋል፡
፡ ፍሬህይወት ያን ጊዜ ገና 22 ዓመቷ ነው፡፡ እሱ
ግን የሚተኛ ሰው ስላልነበር የሚያሸንፉንን ሽማግሌ
የጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን ማህበርተኛችን ትልቅ
ካህን ይዞ መጥቶ እንዲገስፁንና እንዲቆጡን አስደርጎ
በስተመጨረሻ ተሸነፍንለት፡፡ አባቷ እንኳ የዛን ጊዜ
ሁሉ እንቢ ብሎ ነበር፡፡ እኔ ደግሞ ምናልባት ይህን
ያህል ጊዜ ሽማግሌዎች የተመላለሱት ልጄ ፀንሳ
ይሆን እንዴ ብዬ በማሰብ ማታ ስትመጣ ጠብቄ
አጥብቄ ጠየቅኳት፡፡ እሷ ግን ፈፅሞ እንደዚህ
አይነት ነገር ነበር የለም ያለችው፡፡ ከዛ አባትየው
ባይስማማም ቀን ተቆርጦ ያሁሉ እናንተ ባለፈው
ጊዜ የዘረዘራችሁት ሠርግ ተደገሰ፡፡ በመጨረሻም
ሁኔታው አላምር ሲላት ወደ ፍርድ ቤት ሄደች ፡፡
ቁምነገር፡- ፍቺ?
ወ/ሮ ተናኜ፡- አዎ የሱ ሽማግሌዎች ሳይቀሩ
እኛ በዚህ ጉዳይ ውስጥ ከዚህ በኋላ አንገባም
ብለው እስከማለት ደርሰዋል፡፡ በትዳሩ ላይ እንዴት
እንደሚወሰልት ፣የት ሆቴል ከማን ጋር መቼ እንዳደረ
ሁሉ ጠይቃ መረጃ ይዛበታለች፤ ድምፁን ሁሉ
በስልክ ቀድታዋለች፤ እሱ እራሱ ድርጊቱን ከማፈር
ይልቅ በግልፅ ተናግሮታል፡፡
ቁምነገር፡-ምን ብሎ?
ወ/ሮ ተናኜ፡- ያው አንደሚታወቀው የብሎኬት
ማምረቻ አለው፡፡ በተያያዘ የመንግስት ቤቶች አጀንሲ
ጨረታ አሸንፌ ግን ብሩን ሊለቁልኝ አልቻሉም፡
፡ እዚህ ያሉት ሰዎች ጉቦ ካልሰጠኸን ብለው እንቢ
ስላልኳቸው ገንዘቤን ሊያስቀሩብኝ ሲሉ ገንዘቤን
ለማግኘት ስል እዛ የምትሰራና ልታስለቅቅልኝ
የምትችል ልጅ ይዤ በተደጋጋሚ በማደር ላስለቅቅ
ቻልኩ ብሎ የተናገረ ሰው ነው ፡፡ ይሄ እኮ የሚገርም
አይደለም፡፡ ኮንዶም፣ የሴቶች ልብሶች ምን የቀረ ነገር
አለ መኪናው ውስጥ አግኝታበታለች፡፡ ለሽማግሌዎች
እነዚህን ሁሉ ነገሮች ከተናገረች በኋላ ከዚህ በኋላ
ልጆቼን በሰላም ላሳድግ ብላ ነው ወደ ፍርድ ቤት
የሄደችው፡፡
ቁምነገር፡- የእሱ ምላሽ ምን ነበር?
ወ/ሮ ተናኜ፡- በተጋቡ በሁለተኛው አመት
ሌሊት የደበደባት ጊዜ ቤቱ ሄደን እያለ ‹‹ውሰዷት
ልጃችሁን አልፈልጋትም›› ነበር ያለው፡፡ የዛን ጊዜ
እንደውም አንድ ልጅ ወልዳ ሁለተኛውን ቅሪት
ነበረች፡፡ ግን ውሰዷት እያለ ነበር ሲደነፋ የነበረው፡
፡ ፍርድ ቤት ለፍቺ ተከሶ ሲቀርብ ግን ፍቺውን
ለማክሸፍ ያላደረገው ጥረት የለም፤ አልሆን ሲለው
ደግሞ እገላለሁ እያለ ሲዝት ነው የቆየው፡፡
ቁምነገር፡- ፍቺው በፍርድ ቤት ከፀደቀ በኋላ
የንብረት ክፍፍሉስ?

ወ/ሮ ተናኜ፡- ምንም የተከፋፈለችው ንብረት
የለም፡፡ አልፈልግም በጤናዬ ብቻ መውጣት ነው
የምፈልገው ነው ያለችው፡፡
ቁምነገር፡-ለልጆቹ ማሳደጊያስ?
ወ/ሮ ተናኜ፡- የፍርድ ቤቱን ወረቀት ላሳይህ
እችላለሁ፡፡ እኔ ይቅርብኝ ለልጆች ማሳደጊያ ግን
ይስጠኝ በወር 50 ሺህ ብር ያገኛል ብላ በፍርድ
ቤት ስታመለክት የምችለው በአንድ ልጅ 500 ብር
ነው በየወሩ አንድ ሺህ ብር እሰጣለሁ ብሎ ነው
የፀደቀለት፡፡ ለዚያውም ያንን አንድ ሺህ ብር በየወሩ
አይሰጣትም ነበር፡፡
ቁምነገር፡- ራስ አምባ ሆቴል ጋር ያለው ቤት
የእርሱ አለመሆኑ ለፀባቸው ምክንያት እንደሆነ
የሚያውቁ ሰዎች ይናገራሉ፤ ፍሬህይወት የምታውቀው
ነገር ነበር?

ወ/ሮ ተናኜ፡- እኔ ይሄንን አላቅውም፡፡ ቤቱ የሱ
ይሁን የሌላ ሰው ይሁን እኛ የምናውቀው ነገር የለም፡
፡ የእኔ ነው ብሎ ሲያወራ ብቻ ነው የምናውቀው፡
፡ ሰውየው ለነገሩ የማይቀጥፈው ነገር የለም፡፡ ከዚህ
በፊትም ወደዚህ ወደ ሲኤምሲ አካባቢ የሚያሰራ
ህንፃ አጠገብ መኪናውን አቁሞ ፎቶ በማስነሳት
እዚህ እኛ ጋር አምጥቶ በማሳየት ይህ ህንፃ የኔ ነው
በቅርቡ ጨርሼው ወደ እዛ ቤት እንገባለን እያለ
ይነግረን ነበር፡፡ በኋላ ግን ህንፃው የእሱ አለመሆኑን
ደርሰንበታል፡፡ የተባለውም ቤት የሱ ይሁን አይሁን
የምታውቀው ነገር የለም፡፡ ህዝብና መንግስት
ረድተውን ካላጣሩልን በስተቀር አናውቅም፡፡
ቁምነገር፡- ከፍቺ በኋላ ፍሬህይወት ምን ትሰራ
ነበር?

ወ/ሮ ተናኜ፡- አንድ ትንሽ የጉዞ ወኪል ድርጅት
ገና በማቋቋም ላይ ነበረች፡፡ ንግድ ፈቃድ አውጥታ
ቢሮ ገና እያደረጀች ነበር፡፡ ልጆቿ ከሌሎች ልጆች
እንዳያንሱ በትምህርታቸውም በልብሳቸውን
ለመቻል እሷ ቀን ሙሉ ፆሟን እየዋለች ነበር እራሷን
ለመቻል ደፋ ቀና የምትለው፡፡
ቁምነገር፡- ቅዳሜ ቅዳሜ ልጆቹን የሚወስደው
ከየት ነው?

ወ/ሮ ተናኜ፡- ከዚህ ከኛ ቤት ነው የሚወስዳቸው፡
፡ ቀኑን ሙሉ አጫውቶ የሚመልሰው እዚህ ነው፡
፡ እሷ ተከራይታ ነው የምትኖረው፡፡ ከተፋቱ በኋላ
ልታገኘው ስለማትፈልግ ከሁለት ሰዓት በፊት
በጠዋት አምጥታቸው ቶሎ ነው የምትሄደው፡
፡ ማታም መጀመሪያ መምጣቱን በስልክ አረጋግጣ
ነበር መጥታ የምትወስዳቸው፡፡
ቁምነገር፡- በስልክ አይገናኙም ነበር?
ወ/ሮ ተናኜ፡- ፈፅሞ አይገናኙም፤ ከፍቺ በኋላ
አንድ አመት ከስድስት ወር ስልኩንም አንስታ
አታውቅም፤ አታናግረውም፡፡ ልጆቿን ግን ፍርድ
ቤት በወሰነው መሰረት ወስዷቸው ይመልስ ነበር፡፡
ቁምነገር፡- ከግድያው ቀን በፊት የግድያ ዛቻ
በደብዳቤ ፅፎ ልኮ እንደነበር ሰምቻለሁ፤ ምንድን
ነው?

ወ/ሮ ተናኜ፡- በቃሉ በተደጋጋሚ ሲዝት ነበር፡፡
እንደውም የእሷን ታናሽ ወንድም እዚህ አፍሪካ ዳቦ
ቤት ጋር ደውሎ ጠርቶት አንድ ጥይት ይበቃታል
ንገራት ብሎት ነበር፡፡ ይህንን ስንሰማ ምስክሮች
ይዘን በመሄድ ፖሊስ ጣቢያ አመልክተን ነበር፡፡
ያው ምን እንደተባለ አናውቅም ተለቀቀ፡፡ ከግድያው
አንድ ሳምንት በፊት ደግሞ ልጆቹን ወስዶ አጫውቶ
ሲመልሳቸው የአንድ ዓመት ወንዱ ልጅ ኪስ ውስጥ
ደብዳቤ ፅፎ አስቀምጦ ነበር፡፡ ያንን ወረቀት ያገኘነው
ከቀብር በኋላ ቤት ውስጥ ያሉትን ልብሶች ለማጠብ
ስናገላብጥ ነው፡፡ እሷም የዛን ዕለት የልጆቿን ልብስ
ኪስ በደንብ ስላልፈተሸች ነው እንጂ ዛቻውን ልኮላት
ነበር፡፡
ቁምነገር፡-ደብዳቤው ምንድን ነበር የሚለው?
ወ/ሮ ተናኜ፡- በቀደም ዕለት ‹‹ልጆቹን ከትምህርት
ቤት ልትወስጂ የሄድሽ ጊዜ ግንባርሽን ብዬ ልደፋሽ
ነበር ግን፤ ከዛ የተሻለ ሌላ መንገድ ስላለ ጠብቂ ነው››
የሚለው፡፡ (ለቅሶ) የገደላት ዕለትም ለጓደኛው ፃፈ
የተባለ ደብዳቤው ከኪሱ ውስጥ መገኘቱን ፖሊስ
ተናግሯል፡፡ እዚህ ላይ ለመላው የኢትዮጵያ ህዝብ
የምጠይቀው ነገር በእግዚአብሔር ስም ይህቺን የ29 ዓመት
የልጆች እናት በክላሽንኮፍ ጠመንጃ በአደባባይ በጠራራ ፀሐይ
መንግስትና ህዝብ ባለበት ሀገር በግፍ በገደላት ሰው ላይ ፍትህ
እንዲሰጥ ነው፡፡ ሴት ልጅ እናት ነች፣ እህት ነች ፣ ሀገር ነች፡፡
ስለዚህ ህዝቡ ለመንግስት ጩሀቴን እንዲያሰማልኝ በየሀይማኖቱ
ስም ነው የምማፀነው፡፡(ለቅሶ)
ቁምነገር፡- አሉ የተባሉ ንብረቶችም ለማሳገድ ምን
እያደረጋችሁ ነው?

ወ/ሮ ተናኜ ፡- እውነት ለመናገር በዚህ በኩል ምን ማድረግ
እንዳለብንና የት መሄድ እነዳለብን ገና አላውቅንም፤ ሀዘን ላይ
ነው የከረምነው፤ ብሎኬት ማምረቻ የተባለውንም ወደ 20
ክፍሎች ያሉት ቤት፤ መኪናዎችም አሉ የተባሉት ለልጆቿ
ማሳደጊያ ሊሆን ስለሚችል በህግ አግባብ በኩል ምን ማድረግ
እንዳለብን ሙያው ያላቸው ወገኖች ቢረዱንን እንዲተባበሩን
በሴት ልጆቻቸው አምላክ በእህቶቻቸውና በእናቶቻቸው
ስም እለምናለው፡፡ ማንም የሚወዳት ሴት ልጅ ያለው ሁሉ
ይተባበረን ነው የምለው ፡፡
ቁምነገር፡- በእርሶ በኩል ግን ለእንደዚህ አይነት ግድያ
የሚያበቃ የከረረ ፀብ ወይም ምክንያት ብለው የሚገምቱት ነገር
ምንድን ነው?

ወ/ሮ ተናኜ፡- ምቀኝነት ነው፤ ሌላ ምንም ሊሆን
አይችልም፡፡ ከሱ ከተለያየች በኋላ የሱ ሀሳብ ከነልጆቿ ሲርባት
ተመልሳ ከእግሬ ላይ ወድቃ ቤት ትገባለች ነበር፡፡ ቢያይ
አልሆነም፤ አሁን ራሷን ለመቻል ትንሽ ሱቅ ብጤ የትኬት ቢሮ
ለመክፈት ደፋ ቀና ስትል ለምን እራሷን ለመቻል ትሮጣለች
ነው፤ የትኬት ቢሮዋ እኮ ደግሞ ብታያት ገና ምንም ነገር ስራ
ያልተጀመረበት ነው፤ የአየር መንገድ ትኬት የሚሸጥ ሰው
በደንብ ስራን ያውቀዋል፤ ከተገኘም ከአንድ ትኬት ስለሚገኘው
ብር ለዚያውም ትኬት የሚገዛ ሰው ከመጣ ነው፤ ለምን ይሄንን
ከፈተች ነው የሱ ሃሳብ፤ ከዚህ ውጪ ይሄ ነው የሚለው
ምክንያት አይታየኝም ፡፡ ምክንያቱም ከተፋታች በኋላ እንኳን
አምስት ሳንቲም አልጠየቀችውም፡፡ ለልጆቿ በየወሩ ተቆራጭ
መስጠት ያለበትን ብር ሲያስቀር እንኳን ለምን አትለውም፡
፡ አሁን ልጆቿን ለማሳደግ ቀና ደፋ ስትል ቅናት አላስቀምጥ
አለው፡፡ የሱ ሃሳብማ ድሃ ሆና እንድትኖር ነው፡፡
ቁምነገር፡- እርስዎስ ጤናዎት እንዴት ነው?
ወ/ሮ ተናኜ፡- ደህና ነኝ እግዚአብሔር ይመስገን፡፡
ተርፌያለሁ ልጄን ግን ገደላት፡፡
ቁምነገር፡- ከእርሶ ሌላ የተጎዳ ሰው ነበር?
ወ/ሮ ተናኜ፡- አዎ ሁለት መንገደኞች በጥይት ተመትተዋል፡
፡ እንደውም አንዱ ሰውዬ በጣም ተጎድተዋል ተብሏል፡፡ መንገድ
ላይ የነበረ የ10 ዓመት ልጅም ተመትቷል፡፡
ቁምነገር፡- በመጨረሻ የሚገልፁት ነገር ካለ?
ወ/ሮ ተናኜ፡- በአንዳንድ መገናኛ ብዙኃን ላይ ቅሬታ አለን፡፡
እኛ በልጃችን ሞት ሳቢያ ሀዘኑ የእግር እሳት ሆኖብን ሳለ ሃሰተኛ
መረጃ ለህብረሰቡ ያሰራጩብን ጋዜጦችና መፅሔቶች አሉ፡፡
ለምሳሌ ሪፖርተር ጋዜጣ፣ ቆንጆ መፅሔት ንብረት ተካፍላለች
ከሱ በኋላ ልጅ ወልዳለች እያሉ ያቀረቡት ዘገባ መላ ቤተሰቡን
አሳዝኗል፡፡ መረጃውን መጥተው ጠይቀው አረጋግጠው መዘገብ
ሲገባቸው ያልሆነ አሉባልታ ይዘው በመውጣት ህብረተሰቡን
ማደናገራችን ትክክል አይደለም፡፡ እኛ ልጃችንን አንድ ጊዜ
በግፍ ተነጥቀናል፤ ዳግመኛ ታሪኳ መበላሸት የለበትም፤ ብለን
እንዲያርሙ ስንጠይቃቸው የሚያርሙበት መንገድ የሚያሳዝን
ነው፡፡ ሴት ልጅ እንደ ወንድ ልጅ አይደለችም፡፡ ወንድ
በድብቅ ወልዶ ልጅ ሊያመጣ ይችላል፤ ሴት ልጅ ግን ሰው
ሳያያት ልታረግዝነና ልትወልድ አትችልም፡፡ ከሆነም ወለደች
የሚሉትን አምጥተው ቢያሳዩን ጥሩ ነው ፡ ፡አልሆነም እንጂ
ከዚያ ውጪ ከተፋታች በኋላ ብትወልድስ ችግሩ ምንድንነው፡፡
ስለዚህ ሚዲያዎችን እባካችሁ ስለ ሴት ልጅ ብላችሁ እውነታን
አታዛቡ ጠይቃችሁ ፃፉ ነው የምለው፡፡ በማንኛውም መልኩ
የልጃችንን ሀዘን ሊካፈሉንና በህግም በኩል ሊረዱን የሚፈልጉ
ሁሉ በ0911693061 ሊያገኙኝ ይችላሉ፡፡

ቁምነገር፡- አመሰግናለሁ፡፡

ምንጭ ቁምነገር

posted by Gheremew Araghaw

የዜጎችን ገቢ ያላገናዘበው የ40/60 የቤት መርሀ ግብር – ከብስራት ወ/ሚካኤል

ለዛሬ አነጋጋሪ እና ለዜጎች እጅግ ፈታኝ ከሆኑት መካከል መጠለያን (ቤትን) እንመልከት፡፡ በደርግ ሥርዓት ዕድሜው 18 ዓመት የሞላው ማንኛውም ዜጋ በግሉም ይሁን በማህበር ተደራጅቶ እስከ 500 ካሬ ሜትር የከተማ የመኖሪያ ቤት መስሪያ ያገኝ ነበር፡፡ በማኅበር የተደራጀው እና የቀበሌም ሆነ ሌላ መኖሪያ ቤት የሌለው ደግሞ በ20 ዓመት ከ7 ሺህ እስከ 14ሺህ ብር ክፍያ የህንጻ ቤት ባለቤት ተሆኗል፡፡ በዚህም ለቀድሞው የሀገሪቱ ፕሬዝዳንት ኮሎኔል መንግስቱ ኃ/ማርያም ረጅም እድሜና ጤና የሚመኙ የአዲስ አበባ ነዋሪዎች ቀላል አይደሉም፡፡ የቤትና የከተማ ቦታ ባለቤት ሆነዋልና፡፡ አንዳንዶቹም የፕሬዝዳንቱን ፎቶግራፍ ከሳሎናቸው ግድግዳ ላይ ለማስታወሻነት ሰቅለዋል፡፡ በምን መስፈርት እንደሆነ ባይታወቅም መጥመቅ ኢህአዴጋዊያን የቤት መስሪያ ቦታ አሊያም ሌሎች ጥቂቶችን እንደ በረሃ ዛፍ ጣል ጣል በማድረግ የቤት ባለቤት ለማድረግ ሲጣጣር ሌሎች ግን ከቤታቸው ሲፈናቀሉና ሲሰቃዩ አይተናል፡፡

 

ኮንዶሚኒየም ይሰራላችኋል

በከተሞች መጠለያ( ቤት) ለሌላቸው የቤት ባለቤት ለማድረግ እንደተነደፈ የተነገረን ‹‹አዲሱ›› የቤት ልማት ፕሮጀክት በአብዛኛው ማንን ተጠቃሚ እንዳደረገ በየማዘጋጃ ቤቱ ሄዶ ማረጋገጥ ይቻላል፤ችግሩ ዛሬም አልተቀረፈምና፡፡

በርግጥ ይሄ የጋራ መኖሪያ ቤት (ኮንዶሚኒየም) ግንባታ ከዛሬ 7 ዓመት በፊት በ1997 ዓ.ም ሲጀመር በለጋሽ ሀገር ድጋፍ እጅግ ዝቅተኛ ገቢ ያላቸውን በተለይም የጎዳና ተዳዳሪ፣ ጧሪ አልባ አረጋዊያንን እንዲሁም ጎልማሶችን ተጠቃሚ ለማድረግ ነበር፡፡

ነገር ግን በ1997 ዓ.ም በሀገሪቱ የተፈጠረውን ያልተጠበቀ የፖለቲካ ጡዘትን ተከትሎ ኢህአዴግ የቀድሞውን የቅንጅትን እንቅስቃሴ በመፍራት ለፖለቲካ ፍጆታ በተለይም የወቅቱን የምርጫ ድምጽ በመግዛት የከተማ ነዋሪውን የጋራ መኖሪያ ቤት ባለቤት ለማድረግ እንደ ቀልድ ከ400 ሺህ በላይ ነዋሪዎች ሊመዘገቡ ችለዋል፡፡ በዚህም መሰረት ባለፉት 7 ዓመታት ከተመዘገበው ነዋሪ ጋር ሲነፃፀር የተገነባው የቤት ቁጥር ከ15% አይበልጥም፡፡ ቀሪው ተመዝጋቢ ከሰማይ የሚወርድ ፍርፍር ያህል እየጠበቀ ይገኛል፤ በዚህ ሁኔታ በኢህአዴግ አካሄድ ከዛሬ 20 ዓመት በኋላ የሚሳካ አይመስልም፡፡

ከተገነቡ ቤቶች መካከል በስመ እጣ ከተወሰኑ ሰዎች በስተቀር የገዢው ፓርቲ አባላትና ደጋፊዎች የቤት ባለቤት መሆናቸውና በጎን በሚደረግ ህገ ወጥ ምዝገባም ይከናወን እንደነበር የቀድሞ ተመዝጋቢዎች በተለያየ ጊዜ እሮሮ ማሰማታቸው አይዘነጋም፡፡ በተጨማሪም ከዚህ በፊት ተመዝግበው የነበሩ፤ ነገር ግን የስም ዝርዝራቸው ከፋይል ውስጥ የጠፋም እንዳለ በተደጋጋሚ መሰማቱ አይዘነጋም፡፡ ይሄ ደግሞ የገዢው ፓርቲ ግላጭ ባህርይ እንደሆነ በተደጋጋሚ ይነገራል፡፡ ይህ በእንዲህ እንዳለ አዳዲስ ቤት ፈላጊዎች ግን ኦፊሴላዊ በሆነ መንገድ አለመኖሩ ይታወቃል፡፡

40/60 የመኖሪያ ቤት መርሃ ግብር ሲታይ

ይሄ አዲስ መርሃ ግብር የሚለው ደግሞ የመኖሪያ ቤት ፈላጊው ህዝብ የቤት ባለቤት መሆን ከፈለገ የሚፈልገውን የቤት መጠን ጠቅላላ ዋጋ 40% በ5 ዓመት ውስጥ በመቆጠብ 60% በመንግስት በሚመቻች ብድር የቤት ባለቤት መሆን እንደሚቻል ተገልጻDል፡፡ ይህም በ2005 ዓ.ም ይተገበራል ተብሏል፡፡

በ2005 ዓ.ም የመጀመሪያው ምዕራፍ 35 ሺህ ቤቶች እንደሚገነቡና በዛው ዓመትም 10ሺህ ቤቶች እንደሚገነቡ በከንቲባ ኩማ ደመቅሳና በሚኒስትር አቶ መኩሪያ ኃይሌ ይፋ ተደርጓል፡፡ ይገነባሉ የተባሉት ቤቶች በግልፅ እነማንን ታሳቢ እንዳደረጉ በዝርዝር የተገለፀ ነገር የለም፤ በደፈናው ዝቅተኛ ገቢ ያላቸውን ታሳቢ ያደርጋል ቢባልም በተገኘው መረጃ ግን እውን እንደማይሆን ያነጋገርኳቸው አንዳንድ የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎች ይናገራሉ፡፡

 

መንግስት ይፋ ያደረገውን የቤት ዓይነት በየወሩ የሚቆጠበውን የገንዘብ መጠንና ጠቅላላ ዋጋ በጥቂቱ እንይ፡፡ ባለ 1 መኝታ ቤት የሚፈልግ ሰው በየወሩ 857 ብር መቆጠብ ያለበት ሲሆን የቤቱ ጠቅላላ ዋጋ 128,590 ብር ነው፡፡ ባለ2 መኝታ ቤት ፈላጊ ደግሞ በየወሩ 1,337 ብር መቆጠብ ሲኖርበት የቤቱ ጠቅላላ ዋጋ ግን 200,475 ብር ሲሆን ባለ 3 መኝታ ቤት ፈላጊ በየወሩ 2,133 ብር መቆጠብ ያለበት ሲሆን የቤቱ ጠቅላላ ዋጋ ግን 320,000 ብር እንደሆነ ተገልጻDል፡፡ በእነኚህ ዋጋዎች ነው ዝቅተኛ ገቢ ያላቸውንም ያካተተ ነው የሚል መርሃ ግብር ይፋ የተደረገው፡፡

በአሁን ወቅት በኢትዮጵያ ያለውን ዝቅተኛ፣መካከለኛ እና ከፍተኛ ገቢ የሚባሉትን ዜጎች የሚያገኙትንና ወጭ የሚያደርጉትን አማካይ ዋጋ አሀዝ መረጃ ለማግኘት የግድ የዓለምአቀፍ ተቋማትን አሊያም የፈረንጆችን ቤት ማንኳኳት ያስፈልጋል፡፡ ይህን መረጃ ማወቅ ደግሞ ከላይ ከተጠቀሰው አሀዝ እና እውነታ ጋር ለማነጻጸር ይረዳል፡፡መረጃው ደግሞ የሚዘጋጀውና የሚለቀቀው በየ5 ዓመቱ በመሆኑ የሀገሪቱን ተጨባጭ እውነታ ለማረጋገጥ አስቸጋሪ ስለሚሆን ለጊዜው ትቼዋለሁ፡፡

ምናልባት የተባለውን መረጃ በገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር የሚመራው ማዕከላዊ ስታስቲክስ ኤጀንሲ ደግሞ በየዓመቱ የሚፈለገውን ወቅታዊ መረጃ ለመስጠት አይደፍርም፡፡ ይህንንም ለማረጋገጥ ብሄድም ወቅታዊ መረጃ የሚሰጠው በሚኒስቴር መስሪያ ፈቃድ ከተረጋገጠ በኋላ መሆኑን ሳውቅ የተለመደው የመረጃ መጋገር ስራ አለመጠናቀቁን ተረድቼ ተመለስኩ፡፡ በዚህም ምክንያት ለዛሬ ተቀጥረው በደመወዝ የሚተዳደሩትን በቀጥታ በማነጋገር ጥቂቶችን ለመውሰድ ተገድጃለሁ፡፡

በዚህም መሰረት አነስተኛ የትምህርት ደረጃ ያላቸው የጥጉ (የጥበቃ የጉልበት) ሰራተኞች አማካይ ገቢ እስከ 1 ዓመት ስልጠና የምስክር ወረቀት የወር ገቢ ያላቸው ከ800 ብር ደመወዝ፣ የዲፕሎማ ከ1200 ብር፣ የመጀመሪያ ድግሪ ያላቸው 1600 ብር፣ የሁለተኛ ድግሪ ያላቸው 2500 እና የዶክትሬት ድግሪ ያላቸው 3500 ብር አማካይ ወርሃዊ ደመወዝ ያገኛሉ፡፡ ከተጠቀሰው ደመወዝም የስራ ግብር፣ የጡረታ ዋስትና፣ የአባይ፣… ወዘተ እየተባለ ከ15 – 20% እና ከዚያ በላይ የሚቆረጥም አለ፡፡

አንድ ጠንካራ ሰው ከሚያገኘው ከተጣራ ደመወዝ ከወጪ ቀሪ ሊቆጥብ የሚችለው ቢበዛ 1/4ኛውን ቢሆን ነው፡፡ የሚቆጥበውም ለተለያዩ ድንገተኛ እና የረጅም ጊዜ ጠቀሜታ ላላቸው አገልግሎቶች መሆኑ ይታወቃል፡፡ ይሁን እንጂ በዚህ መልኩ እንኳ ቢሆን የ3,500 ብር ደመወዝ የሚያገኝ ሰራተኛ ከወጪ ቀሪ ሊቆጥብ የሚችለው በወር 700 ብር ሲሆን በ40/60 የመኖሪያ ቤት መርሃ ግብር መሰረት ዝቅተኛውን ባለ 1 መኝታ ቤት ባለቤት ለመሆን 875 ብር በየወሩ መቆጠብ የግድ ነው፡፡ በዚህ ሁኔታ ፕሮጀክቱ ማንን ታሳቢ እንደሚያደርግ ዳግም ሊጤን የሚገባው ነው ሲሉ ነዋሪዎች ይገልጻሉ፡፡ ሌላው ገንዘቡ ቢቆጠብ እንኳ የመርሃግብሩ ተፈጻሚነት ላይም ከፍተኛ ጥርጣሬ ያላቸው አሉ፡፡ እዚህ ላይ በአዲስአበባ ዩኒቨርስቲ ቢዝነስና ኢኮኖሚክስ ት/ቤት የኢኮኖሚክስ መምህር እንዳልካቸው በድሉ (ስማቸው የተቀየረ) እንዳሉት ከሆነ እሳቸውም ከላይ የተሰጠውን ጥርጣሬ ይጋራሉ፡፡ ለጥርጣሪያቸው ምክንያት ያደረጉት በአሁን ወቅት መንግስት ያቀዳቸውን እቅዶች ተግባራዊ ለማድረግ ከፍተኛ የገንዘብ እጥረት ስለገጠመው ክፍተቱን ለመሸፈን ባለፉት ሁለትና ሶስት ዓመታት የተለያዩ ገንዘብ መሰብሰቢያ ስልቶችን ተግባራዊ ማድረጉን በማስታወስ አዲሱ 40/60 መርሃ ግብርም ከዛ የተለየ ሊሆን እንደማይችል ያላቸውን እምነት ገልፀዋል፡፡

እዚህ ላይ በአንድ ሚኒስቴር መስሪያ ቤት እየሰሩ እንደሆነ የገለፁት አቶ ተስፋሁንና አቶ ሞገስ በመርሃግብሩ ላይም ተቃውሞ እንዳላቸው ገልጸዋል፡፡ ለዚህም ምክንያት ያሉት መንግስት የከተማው ነዋሪ የአቅሙን ያህል በማህበር ተደራጅቶም ይሁን በግሉ ቤት እንዳይሰራ በሊዝ ስም በአዋጅ የመሬት ጭሰኛ ካደረገ በኋላ ቦታ ከልክሎ ገንዘብ አምጣና ቤት ይሰራልሃል ማለት ‹‹ዶሮን ሲያታልሏት በመጫኛ ጣሏት›› ዓይነት ነው ሲሉ ይከራከራሉ፡፡ ‹‹በተጨማሪም የተጀመረው የጋራ መኖሪያ ቤት (ኮንዶሚኒየም) ሂደት ፍጻሜው አለመታወቁም እንቆቅልሽ ነው፡፡›› ሲሉ ገልፀዋል፡፡ በተለይ አቶ ሞገስና አቶ ተስፋሁን ‹‹በአሁኑ ወቅት የኢህአዴግ መንግስት የሚከተለው የተሳሳተ ፖሊሲ በሀገሪቱ ላይ ትልቅ የፖለቲካ፣ የኢኮኖሚና የማህበራዊ ቀውስ በመፈጠሩ መምራት የማይችልበት ደረጃ ላይ በመድረሱ ሲዳክር ይታያል፤ በዚህም ስህተቱን ለማረም ሌላ ስህተት እየተሰራ እንደሚገኝ እና በየመስሪያ ቤቱም የተረጋጋ ሁኔታ እንደሌለ›› ጠቁመዋል፡፡ ለዚህም ወደሌላ አላስፈላጊ አቅጣጫ ከመሄድ ኢህአዴግ አሁን ሀገሪቱን መምራት አለመቻሉን አምኖ ስልጣኑን በሰላም መልቀቅ አሊያም ማጋራትና አብሮ መስራት እንዳለበት አሳስበዋል፡፡

 

posted by Gheremew Araghaw

ደሮን ሲያታልሏት… በመጫኛ ጣሏት

በወያኔ/ኢህአዴግ ውስጥ የተፈጠረዉ የስልጣን ክፍፍል የፈጠረዉ የእርስ በርስ ሽኩቻ እያየለ መጥቶ ዛሬ አራቱ የእህአዴግ ድርጅቶች ካለመተማመናቸዉ የተነሳ እንኳን አገር መምራት ትናንሽ የፖሊሲ ዉስኔዎችንም በጋራ መወሰን አቅቷቸዋል። “የማይተማመን ባልንጄራ በየወንዙ ይማማላል” እንደሚባለዉ ኦህዴድ፤ ብአዴን፤ ደኢህዴግና ህወሀት ሁሉም ጠ/ሚኒስቴርና ሁሉም ምክትል ጠ/ሚኒስትር መሆን በመፈለጋቸዉ ቦታዉ አልበቃ ሲላቸዉ እራሳቸዉ የጻፉትን ህግመንግስት ደፍጥጠዉ ከሰሞኑ ሦስት ምክትል ጠ/ሚኒስትር በመሾም አገራችን ኢትዮጵያን የሞኞች ድራማ መድረክ አድረገዋታል። ህዝብንና አገርን ያታለሉ እየመሳለቸዉ በተጨባጭ ግን እራሳቸዉን የሚያታልሉት የወያኔ ባለስልጣኖች እራሳቸዉ ጽፈዉ “ህገመንግስት” ብለዉ የሰየሙትን ከፍተኛዉን የአገሪቱን ህግ ጥሰዉ በታሪክ ለመጀመሪያ ግዜ አንድ አገር በአንድ ጠ/ሚኒስትርና በሦስት ምክትል ጠ/ሚኒስትሮች እንዲመራ አድረገዋል።

ሰሞኑን በወያኔ መንደር የታየዉ በሹመት መንበሽበሽ ወያኔዎች ሊነግሩን እንሚፈልጉት ከልማትና ከእድገት ጋር ምንም ግንኙነት ዮዉም። ወያኔ ጠ/ሚኒስትር ከሾመ ከ3ወር በኋላ ሌሎቸ ሁለት ምክትል ጠ/ሚኒስትሮች የሾመዉ በአራቱ አሻንጉሊት ድርጅቶች መካክል የኃ?ማሪያም ደሳለኝን ሹመት ተከትሎ የተፈጠረዉን ኩርፊያና የስልጣን ሽሚያ ለማርገብ አንደሆነ ከማንም የተሰወረ አይደለም። በተለይ በአገሪቱ ዉስጥ የሌለ የስልጣን መዋቅር ተፈልጎለት ምክትል ጠ/ሚኒስት ሆኖ የተሾመዉ የሙክታር ከድር ሹመት ስራ እንዲሰራበት ሳይሆን “ብዙሀኑን ያለቀፈ ዲሞክራሲ ድሞክራሲ አይደለም” በሚል መርህ ዙሪያ ተሰባስበዉ የዉስጥ ለዉስጥ ትግል የጀመሩትን የኦህዴድ አባላት ለማግባባት ነዉ። ሆኖም ትክክለኛዉን የነፃነት ትግል የጀመሩት የኦህዴድ አባላት እንደዚህ አይነቱን “ዶሮን ሲያታልሏት በመጫኛ ጣሏት” የሚሉትን የወያኔ የማጭበርበሪያ ሽፋን ተገንዝበዉ የኦሮሞ ህዝብ የማማባበያ ሳይሆን የትክክለኛ ስልጣን ባለቤት እስኪሆን ድረስ ትግላቸዉን ይቀጥላሉ የሚል የፀና እምነት አለን።

ወያኔ ከሰሞኑ ያደለዉ የስልጣን ራሺን  ኦህዴድ ዉስጥ የተነሳዉን  የስልጣን ይገባኛል  ጥያቄ ያፈነ ከመሰለው እጅግ በጣም ተሳስቷል። ይልቁንም ይህ የስልጣን ረሺን የሚያሳየዉ  ይህ ከእያንዳንዱ ድርጅት የተውጣጣዉ  የጠቅላይ ሚንስትርነት ድሪቶ መአት  ለሀገሪቱ ፈረስ እንሰራለን ብለው ግመል እየሰሩ መሆናቸውን ነዉ። የይህ በዚህ በኮሚቴ በተሰራ ግመል አይሉት ፈረስ ደግሞ ኦህዴድም ሆነ ሌሎቹ ወያኔ ሰራሽ ድርጅቶች አይታለሉም ብለን እናምናል።

ወያኔ ህግመንግስታዊ ስርአቱን በኃይል ለመናድ አገኘኋቸዉ እያለ ስንት ሰላማዊና ህግ አክባሪ ዜጎችን ወደጨለማ ቤት እንደወረወሯቸው የሚያዉቀዉ አባት፤እናት ወይም ልጅ የታሰረበት ቤተሰብ ብቻ ነዉ። ወያኔ ህግመንግስቱን የሚጠቀመዉ ተቃዋሚዎቹን ለማጥቃት ነዉ፤ በሌላ በኩል ደግሞ ወያኔ እሱ እራሱ የጻፈዉን ህግመንግስት ሲያሰኘዉ ይለዉጠዋል፡ የደፈጥጠዋል ወይም ህገመንግስቱ የማይፈቅድለትን ነገር ያደርጋል እንጂ አንድም ቀን ህገመንግስቱን አክብሮ አያዉቅም። ለምሳሌ ባለፈዉ ሳምንት የሾማቸዉ ሁለት ምክትል ጠ/ሚነስትሮች በአገሪቱ ህግመንግስት የኒፈቅዳቸዉ ሹመቶች አይደሉም፤ ሆኖም ወያኔ እርሱን ከህግ በላይ አደርጎ ስለሚያይ ያሰኘዉን ይሾማል ያላሰኘዉን ደግሞ ስላልወደደዉ ብቻ ይሽረዋል።

ለዚህም ነው በወያኔ/ህወሃት ሀገራችን ኢትዮጵያ እየደረሰባት ያለውን ውርደትና እንግልት በመቃወም ስልጣን የህዝብ እንጅ የጥቂት አምባገነኖች  አይደለም በሚል ታጥቀን ይህ አካል ለህግ ተገዥ እንዲሆን ማስገደድ ወይም ማስወገድ አለብን የምንለው። አገራችን ኢትዮጵያ የሚያስፈልጋት ስልጣንን ለብሄር ብሄረሰቦች በኮታ ማደል ሳይሆን እያንዳንዱ ዜጋና እያንዳንዱ ብሄረሰብ መብቱና ነጻነቱ ተከብሮ እራሱን በእራሱ እንዲያሰተዳድር ማድረግ ነዉ። ለዚህ ደግሞ ብቸናዉ መፍትሄ በህዝብ ፍላጎት ላይ የተመሰረተ ዲሞክራሲያዊ ስርዐት መገንባት ነዉ።

የኢትዮጵያን ህዝብ ለስልጣን አበቃነዉ እያሉ የሚፏልሉት የወያኔ ዘረኞች ዘሬ እነሱ እራሳቸዉ  ከፈጠሯቸዉ አሻንጉሊት ድርጅቶች ጋር የስልጣን ሸሚያ ዉስጥ የገቡት የአገሪቱን የጦር ኃይሎች፤ፖሊስ ሰራዊት፤ የደህንነትና የኤኮኖሚ ተቋሞች ሙሉ በሙሉ እየተቆጣጠሩ ነዉ። የወያኔ ፍላጎት አንድ ነዉ፤ እሱም ስልጣን አለ ቦታ ሁሉ ረግ ነዉመቆጣጠርና ሌላዉን ህዝብ ተከታይ ማድረግ ነዉ። ኦህዴድ፤ ብአዴንና ደኢህዴን እነሱ ብዙሃን ሆነዉ ሳለ ከሃያ አመት በላይ የወያኔ ተከታይ ሆነዉ ኖረዋል። ከአሁን በኋላ ግን ቁጥራቸዉንና የሚወክሉትን ህዝብ በሚመጠን መልኩ የፖለቲካ ስልጣን ካልጨበጡ ከወያኔ የኪራይ ቤት ወጥተዉ የራሳቸዉን ቤት መስራት አለባቸዉ።   ከአሁን በኋላ ለኦህዴድ፤ ለብአዴን፤ ለደኢህዴንና ለህወሀትም በሆን ልህልዉናቸዉ የሚበጃቸዉና ከታሪክ ተጠያቂነት የሚያድናቸዉ ከዚህ ሃያንድ አመት ሙሉ ከተጓዙበት አጥፊና አዉዳሚ መንገድ ወጥተዉ ኢትዮጵያ ዉስጥ በእኩልነት ላይ የተመሰረተ ስርአት ገንብተዉ የበደሉትን ህዝብ መከስ ነዉ።

ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ!!

 

posted by Gheremew Araghaw

የባለቤታቸው የቀብር ቦታም ጊዜውን ጠብቆ መፍረሱ የማይቀር ስለሆነ ወይዘሮ አዜብ ከወዲሁ ሊያውቁት ይገባ

ለዚህ ጽሁፍ መነሻ የሆነኝ የሃውልት፤ የመኖሪያ ቤቶችና የመቃብር ሥፍራዎች የማፍረስ ዘመቻ ስለመካሄዱትና ተዛምዶ ስላላቸው ክስተቶች የታዘብኩትን ጽፌ ለማስነበብ ነው። የቀደሞዋ ቀዳማዊት ወ/ሮ አዜብ መስፍን ከቤተ-መንግሥት እንዲለቅቁ ተጠይቀው በተሰጣቸው የጊዜ ገደብ ውስጥ ያላስረከቡበት ምክንያትም ለማነፃፀር እሞክራለሁ።
 የቀደሞዋ ቀዳማዊት ወ/ሮ አዜብ ከባለቤታቸው (አቶ መለስ ዜናዊ) ጋር የኖሩበትን ነጻ የመንግስት መኖሪያ (ቤተ-መንግሥት) ቤት እንዲለቅቁ ተጠይቀው በተሰጣቸው የጊዜ ገደብ ውስጥ ያላሰረከቡበት ምክንያት የተመረጠላቸው ቤት ለደህንነታቸው አመቺ ባለመሆኑ፤ ቤቱን ቢለቅቁ ሃዘኑ ስለሚጫናቸው፤ ዕቃቸውን ለማዘጋጀት ጊዜ ስለሚፈጅባቸው፤ ከፍተኛ የመንግስት በጀት የያዘ የበጎ አድራጎት ድርጅት ሃላፊ ስለሆኑና አሁንም በፓርቲው ውስጥ ባላቸው ተሳትፎ ቤት መልቀቁን በማዘግየታቸው የሥልጣን ሸግግሩን ስመ-ጥሩ ሂደት እያጎድፉት ነው። አዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትሩም ቢሆኑ ጉዳዩን እንዲፋጠን ያላደረጉት የሹመታቸውን ህልውና ይፈታተነው ይሆናል ብለው ስላዩት ግፊት አላደረጉም ወዘተ … በማለት በብዙኀን መድረክ ተተችቶበታል። አሁን ደግሞ ታሪካዊ ሃውልቶች ያሉበት ሥፍራ ይፈለጋል ስለተባለ በሰፊው ቢወሳ ሊያስደንቀን የሚገባ አይመስለኝም። ምክንያቱም የመኖሪያ ቤቶች፤ የመቃብርና የሃውልት ሥፍራዎች ማፍረስና መሰል ለሕዝብ ግልጋሎት የሚሰጡ ተወዳጅ ነገሮችን በመንሳት ዘመቻ ማካሄድ የምዕራባዊያን ገዢ መደብ የሚጠቀሙበት የሕዝብ ትብብር መንሻና ውዥንብር ማካሄጃ ስልት ነው።
ይህን ጉዳይ ስመለከተው በኢትዮጵያ ቀን አቆጣጠር በ2000 ዓ.ም. አካባቢ ውስጥ የመንግስት ቤት ተከራተው በግላቸው እያስጠገኑ፤ በፈረቃ በሚሰጣቸው መብራትና ውሃ እየተገለገሉና ኪራይ በወቅቱ እየከፈሉ ለአመታት ያህል ከመንግስት ተከራይተው የኖሩበትን የመኖሪያ ቤት የቤት ውሉን የፈረሙት ተከራዎች በቤት ውስጥ አይኖሩምበትም፤ ቤቱ አነስተኛ ገቢ ላላቸው ኢትዮጵያውያን ይሰጣል፤ ቤቱን አከራይታችኋል ወዘተ … የሚል ምክንያት እየተሰጣቸው በተወሰነ ቀን ውስጥ ቤቱን ለቅቃችሁ ለመንግስት እንድስታረክቡ፤ ባታስረክቡ ቤቱ ይታሸጋል፤ ብሎም ዕቃችሁ ከቤት ወጥቶ ከመጣሉም በላይ የወጣበት የሰራተኛ ክፍያ ሂሳብ እንድትከፍሉ ትደረጋላችሁ የሚል ከባድ የጽሑፍ ማስጠንቀቂያ ሲደርሳቸው ለክልሉ የቀጠናው ፖሊስና ለክፍለ ከተማው ጽ/ቤቶች እንድያውቁት ሲደረግ ህዝቡ ተደናግጦ በከተማው ውስጥ ትርምስ ተፈጥሮ ነበር። በተራው ህዝብ ላይ የመጣው የቤት ልቀቁ ጣጣ በመንግስት ቤት ለሚኖሩ የኢሕአዴግ አባሎችም ደብዳቤው በስህተት ተጽፎ ደርሷቸው ስለነበር እኛ በሜዳ የታገልነው ይህ በደል እንዲደርስብን አይደለም በማለት በኪራይ ቤት አስተዳዳሪዎችና በጸሐፊዎቻቸው ላይ ሲፎከርባቸው እንደነበር አስታውሳለሁ።
የቤት ልቀቁ ማስጠንቀቂያው በመኖሪያ ቤቶች ጉዳይ ላይ ሳይቆም በመቃብር ቦታ ላይ ሙታን የቀበሩ ግለሰቦችም እንዲሁ አካባቢው ለመንገድ ስለሚፈለግ መቃብሮች ይፈርሳሉና በስፍራው የቀብር ቦታ ያላችሁ በተወሰነ ቀን ውስጥ አስከሬኑን አንስታችሁ ሌላ ቦታ ወስዳችሁ ቅበሩ ተብሎ በይፋ ሲነገር፤ ያላወጡት መቃብሩ በላያቸው ላይ እንዲፈርስ ተደርጎ አጽማቸውን በማዳበሪያ ከረጢት ውስጥ እየተደረገ ለቋሚ ዘመዶቻቸው እንዲሸጥ በማድረግ ህዝቡን በእንባ አራጭተውት ነበር። እንዲሁም ለታሪክ ሊጠበቁ የሚችሉ ቤቶችም በመኖሪ ቦቶች ሳቢያ እንዳይፈርሱ እያለ የኢት.ቅርሳቅርስ ድርጅት ሲወተውት ችላ በማለት የተወሰደውን ወገናዊነት የተሞላውና ህገ ወጥ የሥራ የአፈጻጸም በአገር ውስጥ እንደሚካሄድ ለማያውቁ ግለሰቦች ለማስነበብ ነው።
የቤታቸው መፍረስ/የልቀቁ ማስጠንቀቂያ የደረሳቸው ግለሰቦች ህጋዊ ነዋሪ መሆናቸውን ለማሳወቅና ምትክ የመኖሪያ ቤት ይሰጠን በማለት በኪራይ ቤት ቀጠና ጽሕፈት ቤቶችና የቀጠናው ዋናው አስተዳደርው ቢሮ እየተሰባሰቡ አቤቱታ በማቅረብ እላይ ታች ሲሉ በወቅቱ ያለቀቁትን የነዋሪዎች መኖሪያ ቤት ታሸጎባቸው እቃቸውን ገንዘብ ከፍለው እንዲያወጡ፤ ተከራዮቹ በሌሉበት ቤታቸው ተሰብሮ እቃቸው በፖሊስ ውጭ ተወርብሮባቸው ነበር። ወይዘሮ አዜብ ግን ቤቱን ሲለቅቁ የሚገቡበት ምትክ ቤት ተዘጋጅቶላቸውና ዕቃቸው በክብር ተዘጋጅቶ በውዴታ እንዲለቅቁ ተጠየቁ እንጂ እንደሌላው ተከራይ ነዋሪ ህዝብ ተገድደው አልወጡም።
ተከራዮቹ በግዳጅ ሲፈናቀሉ ካሳ ተከፍሎአቸዋል ለማለት እንዲያስችል ከንብረታቸው ዋጋ በታች ግምት እየተሰጡ ርካሽ የኪራይ ቤት ዋጋ በሚገኝበት የመኖሪያ አካባቢ ሲሄዱ ግማሹም ከርቀቱ የተነሳ ከስራቸው ተፈናቀለዋል። የዕለት መታዳደሪያ ገቢ አጥተዋል። ዘመድ ቤት እንዲዳበሉ ተገድደዋል። ቤተሰባቸውን በትነው የባሰበትም የሜዳ ተዳዳሪ ሆነዋል። በኢህአዴግ አባል በሆኑት ላይ የተላለፈው ውሳኔ ባፈነገጡት አባሎች ላይ ሲጸና ሌሎቹ አልተነኩም። የተለቀቁት ቤቶችም ቤት ለሌላቸው የፖለቲካ አባሎች እንዲሰጥ ተደርጓል።
የእንኝህን ነዋሪ ህዝቦች የደረሰባቸውን እንግልት በተመለከተ የአገር ውስጥ ጋዜጠኞች በሰፊው ጽፈው ሲያወጡ ለዚያን ወቅት የመጻፍ መብታቸው ተጠብቆላቸው ነበር። በየአካባቢው የሚገኘው ሥራ አጥ ዕቃ ጫኝ ወዛደሮች፤ የካሚዮን ባለቤቶች፤ የኪራይ ቤቶች አስተዳደር ባልደረቦች ወገን መግዣና የገቢ ምንጭ ማፍሪያ ሆኖም ነበር።
እነኝህ ነዋሪዎች ሃላፊነታቸውን እየተወጡ እየኖሩ ከቤት ውጡ ሲባሉ እንኳን ቤት የመመምረጥ እድል ሊሰጣቸው ቀርቶ የሚከራይ ቤት ፈልገው ለመግባት በቂ ጊዜ ሳይሰጣቸው ልጆቻቸውን ወልደው ካሳደጉበት ቀየ የተበተኑ ሰዎች አቤቱታቸውን የሚሰማ ጠፍቶ ሲያለቅሱና ሲባዝኑ ይታዩ ነበር። በቀጠናው ጽሕፈት ቤት ግጥር ግቢ የአቤቱታ አቅራቢ በብዛት ተሰባስበው ሲታዩ አስፈቅዳችሁ ሰላማዊ ሰልፍ ውጡ እንጂ ካለፈቃድ በብዛት መሰባሰብ አትችሉም ወይም ጠበቃ አቁማችሁ ክስ መስርቱ ተብለዋል። በአንደኛ ደረጃ ሰላማዊ ሰልፍ ለመውጣት ከህዝብ ደህንነት ጽህፈት ቤት ፈቃድ ለማውጣት ጊዜ ይወስዳል። በሁለተኛ ደረጃ የዜግነት መብቱን የሚያስከብር አስተዳዳሪ ቢኖረው ኖሮ ጉዳያቸው ተሰምቶ በምትኩ ቤት በተሰጣቸው ወይም እንደ ወይዘሮ አዜብ ቤት አግኝተው በፈቃዳቸው እስከሚለቅቁ ጊዜው እንዲራዘም በተደረገ። በሶስተኛ ደረጃ ለጠበቃ የሚከፍሉት የገንዘብ አቅም ቢኖራቸው ከቀጠናው ጽሕፈት ሰራተኞች ጋር በመጨቃጨቅ ጊዜያቸውን ከማጥፋት ቤት ተከራይተው መውጣት በቀለላቸው ነበር።
በተጨማሪም ለወላጆቻቸው ቤት የተከራዩ በውጭ አገር የሚኖሩ ልጆቻቸው ወላጆቻቸውን ለመርዳትና ቤቱን ለማዳን በአስቸካይ ከውጭ አገር የተመለሱ ኢትዮጵያውያን ከወላጆቻቸው ጋር ሄደው ውሉን አድሱልን ብለው ሲጠይቁ ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ደብዳቤ አጽፉ ወይም ከቀጠና ጽሕፈት ቤቶች የተላለፈውን ውሳኔ ለመሻር ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ማዘዣ አምጡ እያሉ የከተማ ኪራይ ቤት አስተዳዳሪ ኃላፊዎች ከቤት ውጣ በተባለው ሕዝብ ላይ ሲመጻደቁና ሲያፌዙበት ነበር። በዚህ አጋጣሚ አንድ ከውጭ መጥቶ የወላጆቹን መበሳጨት የተመለከተና የተማረረ ግለሰብ ሁለተኛ አገር አለኝ ብዬ ወደ እዚች አገር አልመለስም ብሎ በባልስልጣን ፊት ተናገረ ተብሎ ከቅጥር ግቢው በዘበኛ ተባሯል።
ቤት ልቀቁ ብሎ መጠየቅ ወ/ሮ አዜብን ሊያስገርማቸው አይገባም። የመቃብር ሥፍራዎች ማፍረስና አሁን ደግሞ ቦታው ለልማት ይፈለጋል በማለት ሃውልቶችን ለማፍረስ መነሳት ከአገሩ ርቆ ለሚኖር ወገን አዲስ ይሁንበት ይሆናል እንጂ የኢትዮጵያን ሕዝብ አያስደንቀውም። ምክንያቱም በመጀመሪያ ደረጃ የወ/ሮ አዜብ ባለቤት በአመራር ላይ ሳሉ በሕዝብ ላይ የፈጸሙት አንዱ በደል እንደሆነና፤ የባለቤታቸው የቀብር ቦታም እንዲሁ ጊዜውን ጠብቆ መፍረሱ የማይቀር ስለሆነ ወይዘሮ አዜብ ከወዲሁ ሊያውቁት ይገባል። ይሁንና ሕዝቡ በሰላም ከሚኖርበት ቤት የምትክ ቤት ሳይሰጠው አላግባብ ከመኖሪያ ቤትህ በድንገት ውጣ ብሎ ህዝብ ማስገደድ፤ የመቃብር ስፍራዎች፤ የመኖሪያ ቤቶችና ሃውልቶች ለመንገድና ለመንግስት ስራ ጉዳይ ይፈለጋሉ በማለት ንብረት ማፍርስ የሕዝብ መብትና የአገር ቅርሳቅርስ ማውደም የአገር ወዳዱን ህዝብ አዕምሮ እንደሚረብሽ፤ እንደሚያሳዝን፤ ኢትዮጵያዊ ዜጋ መሆንን የሚያስጠላ ኢ-ሰብዓዊነት ድርጊት መሆኑ ገሃድ ነው። ስለሆነም ወ/ሮ አዜብ ከዚህ ገጠመኝ ትምህርት ስላገኙበት፤ ባላቸው ሥልጣንና ተሰሚነት ይህ ዓይነቱን ሕገወጥ የስራ አፈጻጸም ያዘሉ መመሪያዎች እንዲሻሻሉ፤ ባለስልጣኖችም ጉዳዮችን እያመዛዘኑ እንዲወስኑና ወደፊት ከተመሳሳይ ድርጊትም እንዲቆጠቡ የአገር ሃብት እንዲጠበቁ፤ የህዝብ አቤቱታ ሰሚ፤ የአገር ሃብትና ዳር ድንበር ጠባቂ ሆነው መሥራት ይጠበቅባቸዋል።የመኖሪያ ቤትና የመቃብር ሥፍራ ልቀቁ ጣጣ
posted by Gheremew Araghaw

ምሁራንና ‘አክቲቪስቶቻችን’ ሆይ ትግላችን ከመለስ ዜናዊ ወይስ ከሥርዓቱ?

አንዳንድ በትኩሱ ስሜታዊነትን እንዳዘሉ የሚሰነዘሩ ሀሳቦችን ትንሽ ፋታ መስጠትና ማስተዋል የታከለበት የታረመና የተስተክካለሀሳብን መጠበቅ መልካም ምግባር ነው። የጠቅላይ አስለቃሻችን ነብስ ሙታኑን ከተቀላቀሉ በሁዋላ በአሳርና በመከራ ያልታሰበው ሰው ሁሉም ወደሚያስበው ስልጣን ላይ መምጣቱን ተከትሎ የሚሰነዘሩት ሀሳቦች ግን አሁን ድረስ ስክነት አሳይተዋል ብዬ ላስብ አልቻልኩም። ስህተቱ የኔ ከሆነ እዳው ገብስ ነው። የኔ አይነት ሀሳብ ያላቸው ሰዎች ብዙ ከሆኑ ግን መመለስ ያለበት ጥያቄ አለ ማለት ነው።

አቶ ኃይለማርያምን በተመለከተ ከፈጣሪ ጋራ ቀጥታ የግንኙነት መስመር አላቸው ከሚሉን አንስቶ ስለመልካም ባህሪያቸውና የአስተዳደር ችሎታቸው የሚነግሩንን ሰዎች የተለያዩ መድረኮች አስተናግደዋል። ፍትህን እውነትንና ነጻነትን በምድር፣ ሰማያዊ አምላክን ደግሞ ለነብሱ የያዘ ሰው ራሱ ተኩሶ ባይገድል እንኳን በአባሪነትና በተባባሪነት ወንጀል ስሙ ሊነሳ የግድ ነውና እንደምን ሆኖ መልካሙ ሁሉ እንደተቸራቸው ማሰብ ይከብዳል። በአንድ ስርዐት ውስጥ ያገለገለ ሁሉ የግድ ወንጀለኛ ነው ለማለት ፈጽሞ አይደለም።

ነገር ግን የፖለቲካ ስልጣን ይዞ ቁንጮ ሆኖ የተቀመጠና በግድ ያልተመደበ ሰው እሺ ወይም እምቢ የማለት መብት አለውና የማይጠየቅበት ምክንያት የለም። እራሴን ለማዳን ሌሎቹን ማደን ግዴታዬ ነበር የሚል ካለ የፍትህ አካል የሚዳኘው ጉዳይ ይሆናል። የሀገራችን ልሂቃን፣ አክቲቪስቶች፣ ፖለቲከኞች በአብዛኛው ያቀርቡ የነበረው ሀሳብ ወያኔ ወይም የሽፍታው መንግሥት በጉልበቱ ስልጣን ላይ የተቀመጠና ተልዕኮውም አፍራሽ የሆነ ነው የሚል ነው። የዚያ ማስረጃውም ፍትህ የጎደለበት ጎጠኞች እንዳሻቸው የሚፈርዱበትና አሸባሪዎች ተሸባሪዎችን እየከሰሱ ጭለማ ቤት የሚያጉሩበት መሆኑ ነው።

ጥላቻ ባደረባቸው የህብረተሰብ ክፍል ላይ የተነጣጠረ ጥቃት በመፈጸም የዘር ጥፋት የሚያስከትሉ ናቸው። የሀገሪቱን ሉዐላዊነት በማፍረስ፣ የተፈጥሮ ሀብትዋን በመመዝበር ከፍተኛ ዘረፋ ማድረጋቸው፤ በሀገሪቱ ስም ከሚመጣው እርዳታ በላይ ለሁለትና ሶስት መጪ ትውልድ የሚተርፍ ብድር በመበደር አገሪቱን ባለሀብቶች እንዳሻቸው የሚያደርጉበት አደገኛ ሁኔታ መፈጠር፤ የመናገር ብቻ ሳይሆን የማሰብም መብት መነፈግ ነው እያሉ ድህረ ገጾችን አጣበዋል፣ ኮንፈረንስ ላይ ተናግረዋል፣ ሰላማዊ ሰልፍ ላይ መፈክር አሰምተውበታል። ነገር ግን ለዚሁ ሥርአት ትንሽ ፋታ እንስጠው የሚሉት ደግሞ ከዚሁ ወገን ያሉ መሆናቸው ግራ ያጋባል። ምክንያቱም የምንረካው በሰው ለውጥ ወይስ በሥርአት ለውጥ?

ለኃይለማርያም የምንሰጠው ፋታ ለሥርዓቱ የሚሰጥ ፋታ አይደለምን? የሚለው ጥያቄ መመለስ ይገባዋልና ነው።
በዚህ ጉዳይ ውስጥ መሪና ዋናው ተዋናይ ከጠቅላይ አስለቃሹ ቀጥሎ የትግራይ ተገንጣይ ቡድን ነው። አቶ ኃይለማርያም በዚህ ቀመር ውስጥ ምንም ኃይልና ተደማጭነት ያልነበረው ግለሰብ ነው። የፖለቲካ ጡንቻም ያለው ግለሰብ አይደለም። አቶ ኃይለማርያም እውቀቱን ያሰመረበት ጽሁፍ፣ ስለሀገሩ ያለውን ስሜትና እውቀት እንኳን አደባባይ የተናገረበት ነገር አላየሁም። ለሕዝብ የተበተነን ሰለ አቋሙም ሆነ ፖለቲካ ዝንባሌው የሚታወቅ ነገር የለም። የሚታወቀው ነገር የሥርአቱ አሻንጉሊት መሆኑ ነው።

ሀገሬ ኢትዮጵያ ብሎ ለኢትዮጵያውያን በሙሉ ያለውን ፍቅርና መልካም ምኞት የገለጸበት አጋጣሚ ስለመኖሩ የሚታወቅ ነገር ትንሽ ነው። አስተዳደሩ ደግ ስም ያልነበረው አሁንም ተቀባይነት የሌለው ሰው ነው። ታድያ ምን ለመጠበቅ? ምን ለውጥስ በማለምና ምንስ የፖለቲካ ስሌት በማስላት ነው ፋታ እንስጣቸው ራሳቸውን እስኪሆኑ እንጠብቃቸው የሚለው ምርቃት አይሉት እርግማን የሚነገረን?

ታክቲካዊ አይሉት ስትራቴጅያዊ ምክር የሚሰጠን ወደ ምን አይነት ውጤት እንዲያንደረድረን ይሆን?
ምሁራኖቻችንና የፖለቲካው ሞተረኞች ትግሉን ከስርአቱ ላያ ሳይሆን ከመለስ ጋር ብቻ በማድረግ መልሰው እስኪደራጁና እኛን እስኪያንጫጩ ዝም እንበል ማለት ለኛ የተመቸን ተቃዋሚነት እንጂ አሸናፊነት አይደለም አይመስልብንም? የተንገዳገደን ሥርአት ለመጣል ትግል ከማድረግ ይልቅ ትኩረቱ የነበረው አቶ ኃይለማርያም ቢሮ መግባት አልቻሉም፣ ቤተመንግስት አልገቡም ትራፊክ አጨናነቃቸው የሚል ፕሮፓጋንዳ ነው ስንሰማ የነበረው። ቤተመንግስቱ እኮ ቀድሞውንም ቢሆን አይገባውም ነበር።

ኖረበትም አልኖረበትም የሚያመጣው ለውጥ የለም አይኖርምም። መለስ ትልቅ ሀይል ነበር አዎ? ፈላጭ ቆራጭ ነበር? ትክክል። የመለስ ሞት ግን ትግሉን አጠናክሮታል? እንዲያውም። ጉልበቱን አጠናክሮ ለትግል የተበራታ ሀይል በርክቶአል? ምንም። የተደበቁና ዝም ያሉ ሰዎች መድረክ አጨናንቀውበታል? አለን አለን ብለዋል? አዎን እስኪታከተን ድረስ። አሁንስ አሉ? ጋደም ብለዋል።

ወያኔ አቶ ኃይለማርያምን ይዞ እየተደላደለ ነው? በትክክል። ታድያ አቅጣጫችን ምንድን ነው? የማሸነፍ ተስፋ ሕዝባችን ውስጥ እየታየ ነው? እና የኛ ልሂቃን እስከመቼ ነው ለኃይለማርያም ፋታ እንድንሰጠው የሚነግሩን?
አቶ ኃይለማርያም ስልጣን ላይ ከወጡበት ጊዜ ጀምሮ ስዎች ተፈናቅለዋል? በመቶ ሺህዎች። ቤቶች ፈርሰዋል? አዎን በቡልዶዘር!!
ታሪካዊ ቦታዎች ተደፍረዋል? አዎ የአቡነ ጴጥሮስና የሚኒሊክ ሀውልት ሊፈርሱ መሆኑን ሰምተናል። መለስ ትግራይን የማሳደግ ስትራቴጂ መንደፉ ይፋ ሆኖአል? አዎ። ኃይለማርያም የመለስ ዜናዊ ራዕይ አስፈጻሚ ነኝ ብሎናል? አዎ በኩራት። አፈናና እስር ተንሰራፍቶአል? በሚገባ። ጋዜጠኞችን አሸባሪዎች ብለዋል? አዎን። ኃይለማርያም አደባባይ እግዚአብሄርን ከጠራበት ለመለስ ዜናዊ ፍጹማዊና ዘለአለማዊነት የመሰከረበት አይበልጥም? እንዴታ!! ታድያ የምንጠብቀው ምንድን ነው? ትግላችን ከዘረኛውና ከአፍራሹ ሥርዓት ጋር ከሆነ አዘናጊ ምክሮች መቅረባቸውና ወደ ዝምታ መመለሱ የስቃይ ቋጠሮን ማጥበቅ ነው እላለሁ። ምሁራንና ፖለቲከኞች ሆይ በሀሳባችሁ እንዳሰራችሁን በእውቀታችሁ ደግሞ ፍቱን።
ዳኛቸው ቢያድግልኝ
biyadegelgne@hotmail.com

posted by Gheremew Araghaw

The Growing Inequality in Ethiopia (By Solomon Gebre-Selassie)

ድሃ ወዴት ይድረስ?
ምን ሁን ነዉ ምትሉት፤
ምን ይፍጠርላችሁ፤
ምን አርግ ነዉ እሱ ምን ይሁንላችሁ?
እስ በሱ ተዛዝኖ ረሃቡን ታግሶ፤
የናንተን ቁራጭ ቁርጥራጩን ለብሶ፤
ፍርፋሪያችሁን ከመሬት ላይ ለቅሞ፤
በእንጥፍጣፊያችሁ ምላሱን አርሶ፤

Read more:

http://abbaymedia.com/2012/12/04/the-growing-inequality-in-ethiopia-by-solomon-gebre-selassie/

 

posted by Gheremew Araghaw

እሾህን ሳያስወግዱ እንደ ልብ አይራመዱ (ኢሕአፓ)

http://www.ethiolion.com/

posted by Gheremew Araghaw

Post Navigation

Follow

Get every new post delivered to your Inbox.

Join 4,735 other followers

%d bloggers like this: